በአለማችን ውዱ የዱባይ የማራቶን ውድድር በሁለቱም ጾታ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችን የሚያቆማቸው አልተገኘም፡፡ የሽልማት ገንዘብ እና በአለም ላይ ካሉ ትልልቅ ውድድሮች ሜዳማ የሆነው የዱባይ ማራቶን ዛሬ ማለዳ የተደረገ ሲሆን ኢትዮጵያዊው ፀጋዬ መኮንን በ2፡04፡32 በሆነ ሰአት በማሸነፍ የ4 ሚሊየን ብር ሽልማት አሸናፊ ሆነ፡፡
በውድድሩ በወንዶች ኢትዮጵያዊን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ተከታትለው ገብተዋል፣ ማርቆስ ገነቴ ሁለተኛ፣ ግርማይ ብርሀኑ ሶስተኛ፣ ታምራት ቶላ አራተኛ፣ አዝመራው በቀለ አምስተኛ ወጥተዋል ፡፡
በዱባዩ ልዑል ሼክ ሀምዳን ቢን መሀመድ ቢን ራሺድ አል መክቱም የበላይ ጠባቂነት በተደረገው የአለማችን ውዱ ውድድር 20 ሺህ አትሌቶች ተሳትፈውበታል፣ በሴቶቹም ምድብ ከአንደኛ እስከ ዘጠነኛ ተከታትለው ገብተዋል ፡፡
በቀዳሚነት ሙሉ ሰቦቃ በ2፡25፡01 ስተገባ መሰለች መልካሙ በ2፡25፡23 ሁለተኛ ፍሬህይወት ዳዶ በ2፡25፡53 ሶስተኛ ሲወጡ እስከ ዘጠነኛ ደረጃ ያለውንም ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተከታትለው ገብተዋል ፡፡ ዘጠነኛ ላይ ቱርካዊቷን አትሌት ተከትለውም ከአስረኛ እስከ አስራ ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል ፡፡
ምንጭ ፦ gulfnews.com እና ድሬ ቲዩብ
No comments:
Post a Comment