የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የ2020
የአፍሪካ ቢዝነስ ሥራ አመራር ሽልማት አሸናፊ ሆኑ።
አቶ መላኩ ለዚህ የላቀ ሽልማት የበቁት የንግድና ኢንዱስትሪ አጠቃላይ መዋቅሩን ከፌዴራል እስከ ክልል እና ከተማ አስተዳደር ድረስ በማነቃነቅ በሀገር ደረጃ የተረጋጋ የግብይት ሥርዓት እንዲፈጠር በመሥራታቸው መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ አያይዞም ለኮቪድ-19 ተጽዕኖ የማይበገርና የሰከነ ንግድና ኢኮኖሚ እንዲኖር፣ የሀገር ውስጥ ንግድ እንዲያንሰራራ፣ ሀገራዊ የኤክስፖርት ንግድ እንዲነቃቃ በማድረጋቸው መሆኑንም አመልክቷል። አቶ መላኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ግብዓቶችን እንዲያመርቱ በማድረግ አርአያነት ያለውን አመራር በመስጠታቸው መሆኑም ተገልጿል።
ሽልማቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሴክተር አመራሮችና ሠራተኞች የጋራ ጥረት፣ የንግዱ ማኅበረሰብና የአምራች ኢንዱስትሪ ተዋናዮች ከፍተኛ ተሳትፎና ትብብር ውጤት እንደሆነም ተመልክቷል።
የአፍሪካ ቢዝነስ ሥራ አመራር ሽልማት በተቋም፣ በሀገርና በአህጉር ደረጃ በቢዝነስ አመራር በላቀ ደረጃ ውጤታማ ለሆኑ ጥቂት መሪዎች የሚበረከት የመልካም ተግባር ዕውቅና ሽልማት መሆኑን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
No comments:
Post a Comment