ድርጅቱ ደረጃውን የሚያወጣው የየሀገራቱ ክለቦች በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ውድድሮች በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ባለፈው ዓመት ከተሰጠው የ110ኛ ደረጃ በዚህ ዓመት 3 ደረጃዎችን ማሻሻል ችሏል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደረጃ ከወጣላቸው ሀገራት 18ቱን በመብለጥ ነው የ107ኛ ደረጃ የተሰጠው፡፡ በድርጅቱ ሪፖርት መሰፈርት የስፔን ላሊጋ ቀዳሚውን ሲይዝ፣ የእንግሊዝ ፕሪምር ሊግ ደግሞ ተከታይ ደረጃን ይዟል፡፡ የጀርመን ፣ ጣሊያንና ብራዚል ሊግም በቀደም ተከተል ከ3-5ኛ ደረጃ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከአፍሪካ ሀገሮች በሊጋቸው ቀዳሚ ስፍራ የተሰጣቸው ቱኒዚያ፣ ግብጽና ናይጀሪያ ናቸው፡፡ሩዋንዳ፣ ቶጎ፣ ሴኔጋልና ኡጋንዳ በቀደም ተከትል ደካማ ሊግ ያላቸው ሀገሮች በመባል ተቀምጠዋል፡፡
No comments:
Post a Comment