የበጋ
ወቅት አልፎ በበልግ ወቅት ላይ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል “ኢሬቻ ቱሉ” ይባላል፡፡ይህም በበጋ ወቅት ሰው እና እንሰሳት በድርቅ
ሲጠቁ ወይም ሲጎዱ ወደ ተራራ በመውጣት የበልግ ዝናብ እንዲዘንብላቸው ፈጣሪን የሚለማመኑበት ስርዓት ነው፡፡
ክረምት አልፎ በፀደይ መግቢያ ወቅት ላይ በቢሸፍቱ ከተማ - (ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በአዲስ አበባ) በድምቀት የሚከበረው ደግሞ “ኢሬቻ መልካ” ይባላል፡፡ ይህ በዓል ከክረምት ወደ በጋ በሰላም ስላሸጋገራቸው እርጥብ ሳር እና አደይ አበባ በመያዝ ወንዝ ዳር ወጥተው ፈጣሪን የሚያመሰግኑበት ስርዓት ነው፡፡ በዚህ በዓል ላይም ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ በርካታ ሰዎች የሚሳተፉበት በመሆኑ እንደ አንድ የቱሪዝም መዳረሻም ሆኗል፡፡
በዚህ በዓል ላይ ከህፃን እስከ አዋቂ ፣ ሴት ወንድ ሳይል ሁሉም በባህል አልባሳት አምረው እና ደምቀው ያከብራሉ፡፡ ሴቶች ደግሞ ከባህል አልባሳታቸው ባሻገር ስንቄን ይይዛሉ፡፡ ስንቄ በኦሮሞ ሴቶች ዘንድ ትልቅ ቦታ አላት፡፡ በተለይም የአርሲ እና የባሌ ሴቶች ሲዳሩ ከቤተሰቦቻቸው ፣ በክብር ተዘጋጅቶ የሚሰጣቸው ስጦታ ቢኖር ስንቄ ናት፡፡ ስንቄ የሴቶች መብት ማስከበሪያ ቀጭን በትር ናት፡፡ እናቶች ከቆዳ የተሰሩ አልባሳትን ለብሰው ፣ በአንገታቸው ጌጣጌጦችን አጥልቀው ፣ በእጃቸው ከእንጨት የተዘጋጀችውን ቀጭን በትር ይይዛሉ/ስንቄን ማለት ነው/፡፡
ስንቄ የተጣላን
ማስታረቂያ፣ የሴቶች መብት ማስከበሪያ እና ሰላም እንዲሰፍን ማድረጊያ ናት፡፡ በመሆኑም በኦሮሞ ማህበረሰብ ዘንድ ለስንቄ
የተለየ ቦታ እና ከበሬታ ይሰጣል፡፡ ለመነሻ ያህል እኔ ይህን ካጋራኋችሁ ቀሪውን እናንተ ጨምሩበት …..
No comments:
Post a Comment