የዓለም አቀፉ የኑክሌር ፍንዳታ እገዳ ድርጅት በኢትዮጵያ ምርምሮችን ለማከናወን ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
የዓለም አቀፉ የኑክሌር ፍንዳታ እገዳ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ የመረጃ ማዕከል በማቋቋም ምርምሮችን ለማከናወን ፍላጎት እንዳለው ገለፀ፡፡ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ላሲና ዜርቦን ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሯ ደሚቱ ሃምቢሶ ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተወያይተዋል።
ማዕከሉ የኒውክሌር ፍንዳታን፣ እሳተገሞራ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመተንበይ የሚያስችል ተግባራትን ያከናውናል፡፡
ድርጅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚሰበስበው የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች መረጃ ለሚሰጠው አገልግሎት ጥራት እንደሚጠቅመው ተገልጿል። ኢትዮጵያ ደግሞ መረጃን ጨምሮ የድርጅቱን የቴክኒክና የስልጠና ድጋፍ እንድታገኝ ያሰችላታል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
No comments:
Post a Comment