የአለም አገር አቋራጭ ውድድር የብር ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነችው ህይወት አያሌው በ27 ደቂቃ 18 ሰከንድ ቀዳሚ ስትሆን የሀገራ ልጅ አለሚቱ ሀሮዬ በ27 ደቂቃ 23 ሰከንድ ሁለተኛ ስትወጣ ኬንዊያቷ ሜርሲ ችሩኖ በ27 ደቂቃ 36 ሰከንድ ሶስተኛ ሆናለች፡፡
ኢትዮጵያዊቷ ትርሀስ ገብሬ በ28 ደቂቃ 06 ሰከንድ አራተኛ በመሆን ውድድራን አጠናቃለች፣ ህይወት ከውድድሩ በሁዋላ “ይህን ውድድር በተከታታይ ማሸነፍ ፍፁም ድንቅ ነው፣” ያለችው ከ2007 የገለቴ ቡርቃ ድል ወዲህ በውድድሩ በማሸነፍ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ የሆነችው ህይወት “በተከታታይ ለአምስተኛ ጊዜ ማሸነፌ ነው በአለም አቀፍ ደረጃ በተከታታይ ውድድር ሳሸንፍ የመጀመሪያ ነው” ብላለች፡፤
በወንዶቹ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር ኬንያዊው ፖል ታንዊ አሸንፎአል፡፡ በህንድ ሙምባይ በተደረገ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ድንቅነሽ መካሻ በ2 ሰአት ከ28 ደቂቃ ከ08 ሰከንድ አሸናፊ ሆናለች ድንቅነሽን ተከትላ ኬንያዊቷ ግላዲስ ኪፕሶይ ሁለተኛ ስትወጣ ኢትዮጵያዊቷ ብዙነሽ ኡርጌሳ በ2ሰአት 30 ሰከንድ ሶስተኛ ወጥታለች፡፡ ድንቅነሽ አሸናፊ በመሆኗ የ41 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆናለች፡፡
ምንጭ ፡- ድሬ ቲዩብ
No comments:
Post a Comment