የ2013 የዓለም ኮከብ ተጨዋች ክብርን ከሳምንት በፊት በፊፋ
የተቀናጀው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቱጋል ጀግኖች የሚበረከተውን የንጉስ ሄነሪ ሽልማት ጥር 12/2006 በሊዝበን
ተበርክቶለታል፡፡
የሪያል ማድሪዱ እና የዓለም ኮከቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፖርቱጋል ቤተመንግስት በመገኘት ከፖርቱጋል ፐሬዝዳንት አኒባል ኬባኮ ሲልቫ እጅ ሜዳሊያና ሪቫን ተቀብሏል፡፡ ሽልማቱ ለክለቤና ለሀገሬ የበለጠ ጠንክሬ በመስራት ብዙ ድሎችን እንዳገኝ ያበረታታኛል ሲል ሮናልዶ ከሽልማቱ በኋላ ተናግሯል፡፡
የሪያል ማድሪዱ እና የዓለም ኮከቡ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በፖርቱጋል ቤተመንግስት በመገኘት ከፖርቱጋል ፐሬዝዳንት አኒባል ኬባኮ ሲልቫ እጅ ሜዳሊያና ሪቫን ተቀብሏል፡፡ ሽልማቱ ለክለቤና ለሀገሬ የበለጠ ጠንክሬ በመስራት ብዙ ድሎችን እንዳገኝ ያበረታታኛል ሲል ሮናልዶ ከሽልማቱ በኋላ ተናግሯል፡፡
ሮናልዶ የዲስፕሊን፣ ጠንካራ የስራ ባህሪና የማሸነፍ ወኔ ባለቤት መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ በሽልማቱ ስነ ስርዓት ላይ
የሮናልዶን ቤተሰቦች ጨምሮ፣ የስፔን አምባሳደሮች፣ የሪያል ማድሪድ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ፣ የፖርቱጋል አሰልጣኝ ፓውሎ
ፔንቶ እና ሌሎችም ተገኝተዋል፡፡
ምንጭ: foxsports.com
No comments:
Post a Comment