Wednesday, January 29, 2014

ኢትዮጵያ በትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገቧ ተመረጠች

  
   ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት  በትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ሀገራት አንዷ ሆና ተመረጠች። በዓለማችን በአሁኑ ወቅት 57 ሚሊዮን የሚጠጋው የህብረተሰብ ክፍል የትምህርት እድል አላገኘም ከዚህ ውስጥ 54 በመቶውን የሚሸፍኑት ደግሞ አፍሪካውያን ናቸው። ከትምህርት ሽፋን ጋር በተያያዘ አትዮጵያ 20 ዓመታት በፊት 23 በመቶ የነበረውን ሽፋን አሁን ላይ 94 በመቶ ማድረስ ችላለች። 

      በሪፖርቱ  ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምዕተ ዓመቱን ግብ ያሳካኩ ከተባሉት 11 ሀገራት አንዷ ሆና የተመረጠችው ለትምህርት ከፍተኛ ትኩረት ስጥታ በመስራቷ፣  የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ሽፋንን 94 በመቶ ማደረሷና በሁለተኛና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ደረጃም ከሌሎች ሀገራት የተሻለ አፈጻጸም በማሳየቷ መሆኑ ተገልጿል።

   የኢፌዲሪ /ጠቅላይ ሚንስትር  አቶ ደመቀ መኮንን ሁለተኛው የትምህርት ለሁሉም አለም አቀፍ ክትትል ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ሀገሪቱ ይህንን ውጤት ያስመዘገበችው ለትምህርት መስክ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ በመሰራቷ ነው ብለዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ኢትዮጰያ የምዕተ አመቱን የትምህርት ለሁሉም መርሀ ግብር የማሳከላት እድል እንዳላትም ነው የተናገሩት

   በሪፖርቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የትምህርት ለሁሉም አተገባበር ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ የምዕተ ዓመቱን እቅድ ለማሳካት የመምህራንን አቅም በማሳደግና በማጎልበት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ኢትዮጵያ የራሷን እቅድ ነድፋ በመስራት ላይ ትገኛለች ብለዋል። በሪፖርቱ የመምህራንን አቅም ማሳደግና ማጎልበት በገጠር ለሚሰሩ መምህራን ማበረታቻዎችን ማመቻቸት እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
                                                   
                                                ምንጭ ፡- ኤፍ. ቢ. ሲ

No comments:

Post a Comment