“ይህን የመሰለ በጣም ምርጥ ታሪክ ባማረ መልኩ በፈጠራ ብቃት ተውቦ ማየት መሳጭ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የአካባቢን ባህል አክብሮ የህግ እርምጃዎችን መውሰድ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ያሳያል” ብላለች አንጀሊና ጆሊ፡፡
አንጀሊና ጆሊ እ.ጎ.አ በ2005 ዛሃራ የተሰኘች ሴት ልጅ ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ መልክ መውሰዷ ይታወሳል፡፡
በጠለፋ ዙሪያ የሚያጠነጥነው ይህ ፊልም በሰንዳንስ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ከዓለም ዙሪያ ከመጡ ፊልሞች ጋር በድራማ ዘርፍ ውድድር ላይ በመብቃት ለምርቃት ይበቃል፡፡ የኦስካር አሸናፊዋ ድንቅ ተዋናይት አንጀሊና ጆሊ በዘረሰናይ ብርሃነ መሃሪ የተዘጋጀውን ይህን ‘ድፍረት’ የተሰኘ ፊልም፣ “ለኢትዮጵያ ኪነጥበብ ትልቅ ክስተት” ስትል አሞግሳዋለች፡፡
ምንጭ ፡- ድሬ ቲዩብ
No comments:
Post a Comment