Wednesday, May 28, 2014

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በካናዳ በተካሄደው የማራቶን ሩጫ አሸነፉ።



   በወንዶች ማራቶን የማነ ፀጋዬ፣ በሴቶቹ ደግሞ ትግስት ቱፋ አሸናፊ ሆነዋል። አሸናፊዎቹ በማሸነፋቸው 20 ሺህ ዶላር፣ ክብረወሰን በማሻሻላቸው ደግሞ 10 ሺህ ዶላር እና የመኪና ተሸላሚ ይሆናሉ

  አትሌት የማነ ጸጋዬ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት 6 ደቂቃ 54 ሰከንድ ወስዶበታል። የቦታውን ሰዓትም 51 ሰከንድ አሻሽሏል። ውድድሩን በሁለተኝነት ያጠናቀቀው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሙሉጌታ ዋሚ 2 ሰዓት 8 ደቂቃ 18 ሰከንድ ውድድሩን አጠናቋል። ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን የጨረሰው ኬኔያዊው ቼምታን ኢሺምኤል ቡሼንዲች ሲሆን ከሙሉጌታ 17 ሰከንድ ዘግይቶ ገብቷል።

  በሴቶቹ በኩል በተደረገ የማራቶን ውድድርም ኢትዮጵያዊቷ ትግስት ቱፋ እንደ ወንዶቹ ሁሉ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለችበሴቶቹ አንደኛ የሆነችው ትግስት ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት 24 ደቂቃ 30 ሰከንድ ወስዶባታል። 2 ሰዓት 27 ደቂቃ 25 ሰከንድ ሁለተኛ የሆነችው ሌላዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት መሰረት ቶላዋቅ ነች። በሶስተኛነት ውድድሯን ያጠናቀቀችው ኬንያዊቷ ኤጅነስ ኪፕሮፕ ናት።በውድድሩ ከአራተኛ እስከ ስድስተኛ ያለው ደረጃም በኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ተይዟል፡፡

No comments:

Post a Comment