Sunday, May 18, 2014

የአርቲስት ክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ሁለት መኪኖች እንዲሸጡ ፍርድ ቤት ወሰነ፡፡


  በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ከ 50 አመታት በላይ ተወዳጅነትን ይዞ የቆየው የአርቲስት ጥላሁን ገሰሰ መኪኖች እንዲሸጡ ፍርድ ቤት መወሰኑን ሸገር የሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል፡፡

      ለመኪኖቹ መሸጥ ምክንያት ሆኖ የቀረበው የአርቲስቱ የቀድሞው የትዳር አጋር በሆኑት በወ/ሮ ማርታ ሲሚንቶስ በትዳር ወቅት የፈሩ ንብረቶችን የመካፈል ጥያቄ በማንሳት ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በማመልከታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

  ፍ/ቤቱም ጉዳዩን በመከታተል የአርቲስቱ 2 መኪኖች በጨረታ መነሻ ዋጋ 380 ሺህ ብር እንዲሸጡ እና ክፍፍል እንዲደረግባቸው ወስኗል፡፡ Court Orders for Tilahun Gesesse's Cars to be Sold ... Listen at ...http://diretu.be/437377 |

No comments:

Post a Comment