Saturday, May 17, 2014

የቅድመ ታሪክ ሕይወት አጥኚ ፓሊዮንቶሎጂስቶች እስከዛሬ በምድር ላይ ከነበሩ እንስሳት ሁሉ እጅግ ግዙፉ የተባለውን የዳይኖሰር ዝርያ ቅሪተ አካል (አጽም) ማግኘታቸው ተሰማ፡፡

ቀና አድርጎ በሚቆምበት ጊዜ 20 ሜትር ወይም በአማካይ ቁመቱ የሰባት ፎቅን ያህል እንደነበር ተገልጿል፡፡ አሁን የተገኘው ይህ ዳይኖሰር ከዚህ በፊት ያልታወቀ አዲስ ዝርያ መሆኑና እስካሁን ድረስም ስም አንዳልወጣለት ታውቋል፡፡

     አርጀንቲና ውስጥ በአንድ ገበሬ በአጋጣሚ የተገኘው የዚህ የዳይኖሰር ቅሪተ አካል (Fossilized Bones) ላይና በአካባቢዊ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ዳይኖረሱ ከዛሬ 95 እስከ 100 ሚሊየን ዓመታት ግድም በምድራችን ላይ መኖሩ ታውቋል፡፡ይህ ግዙፍ ዳይኖሰር ክብደቱ 77 ቶን ወይም 14 የአፍሪካ ዝሆኖችን የሚያክል ሲሆን፣ ከጭንቅላቱ እስከ ጅራቱ ድረስ ደግሞ 40 ሜትር ርዝመት እንደነበረው ቅሪተ አካሉ ላይ የተደረገ ጥናት ይጠቁማል፡፡ ዳይኖሰሩ አንገቱን

       ዳይኖሰሮች ከዛሬ 231.4 ሚሊየን ዓመታት አንስቶ በምድር ላይ ለበርካታ ሚሊየን ዓመታት የኖሩና የዛሬ 66 ሚሊየን ዓመታት ግድም ድንገት የጠፉ ጥንታዊ እንስሳት ናቸው፡፡ በበርካታ የዓለማችን ክፍሎች እጅግ በርካታ የዳይኖሰር ቅሪተ አካል በተለያየ ጊዜ መገኘቱ ይታወቃል፡፡

No comments:

Post a Comment