Tuesday, May 27, 2014

ቅዱስ ጊዮርጊስ የ2006 ፕሪሜየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ


 21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ይርጋለም ላይ ከሲዳማ ቡና ጋር የተጫወተው ቅዱስ ጊዮርጊስ በፍፁም ገብረ ማርያም ብቸኛ ግብ 10 አሸንፏል በዚህም ምክንያት 5 ጨዋታ እየቀረው 2006 የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱን አረጋግጧል። ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ 21 ጨዋታ 58 ነጥብ በመያዝ ሻምፒዮን ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና 20 ጨዋታና 38 ነጥብ ሁለተኛ ሆኗል፡፡

ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ኢትዮጵያ መድህንን አስተናግዶ 1አቻ ተለያይቷል፡፡ አዲስ አዳጊው ወላይታ ድቻ የወራጅ ስጋት የሚታይበትን ሙገር ሲሚንቶ በሜዳው አስተናግዶ1ለ0 ማሸነፍ ችሏል፡፡በመውረድ ስጋት ውስጥ የሚገኘው ዳሽን ቢራ በበኩሉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አዲስ አበባ ስታዲዮም ላይ 1ለ0 በመርታት ሁለተኛ ተከታታይ ወሳኝ ድሉን አስመዝግቧል፡፡
 የኢትዮጵያ ቡና እና አርባምንጭ ከነማ በአበበ ቢቄላ ስታዲዮም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ያደረጉት ጨዋታ ሊጠናቀቅ 22 ደቂቃዎች ሲቀሩት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት ተቋርጧል ፡፡ በጨዋታው አርባምንጭ ከነማ ከእረፍት በፊት በገብረሚካኤል ያእቆብ ባስቆጠራት ግብ አንድ ለዜሮ እየመራ መዝለቅ ችሎ ነበር፡፡

  የተወሰን ደቂቃ ሲቀረው የተቋርጦ የኢትዮጵያ ቡና እና የአርባ ምንጭ ከነማ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዶ ኢትዮጵያ ቡና በቶክ ጀምስ አማካኝነት ግብ በማስቆጠር 1 1 የአቻ ውጤት ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡ መከላከያና ደደቢት የሚያደርጉት የሳምንቱ የጨዋታ መርሃ ግብር ደግሞ  መከላከያ ወደ ሱዳን በማምራቱ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡ 

No comments:

Post a Comment