Monday, May 26, 2014

በ2014ቱ የአለም የዱላ ቅብብል ውድድር ኢትዮጵያ በወንዶች 4 በ1500 ሜትር ሶስተኛ ሆና አጠናቀቀች


   በባሃማሷ ናሱ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የአለም የዱላ ቅብብል የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያ በወንዶች 4 1500 ሜትር በሶስተኝነት አጠናቀቀች። የኬንያ አትሌቶች 14 ደቂቃ 22.22 ሰከንድ  የአለም ሪከርድን በሰበሩበት በዚህ ውድድር አሜሪካውያን የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ሁለተኛ በመሆን ጨርሰዋል።

 ብርቱ ፉክክር ያደረጉት ኢትዮጵያውያኑም ውድድሩን 14 ደቂቃ 41.22 ሰከንድ በማጠናቀቅ የሀገራቸውን ሪከርድ ማሻሻል ችለዋል። በዚህ ውድድር ጃማይካውያን በወንዶች 4 200 ሜትር እንዲሁም ኬንያውያን በሴቶች 4 1500 ሜትር የዱላ ቅብብል አዲስ የአለም ክብረ ወሰን አስመዝግበዋል። 4 100 እና 4 400 ሜትር ውድድር 1 እስከ 8 ያጠናቀቁት አትሌቶች 2015 . በቤጂንግ ለሚደረገው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቀጥታ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

No comments:

Post a Comment