Wednesday, March 18, 2020

ከቢራ ጣዕምና ይዘት መጓደል ጋር በተያያዘ ከዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ የተሰጠ መግለጫ

  
ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ላለፉት 20 ዓመት ኢትዮጵያዊያን ደንበኞቹን ስኬታማ በሆነ መንገድ ሲያገለግል የቆየ ፋብሪካ ሲሆን በኢትዮጵያ በጥራቱ ተመራጭ ቢራ በመሆን በበርካቶች ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ነው፡፡ ፋብሪካው የሚያመርተው የዳሽን ቢራ ምርት በአብዛኛው ከኢትዮጵያውያን አርሶአደሮች በሚገኝ ግብዓት ሙሉ በሙሉ (100%) ከገብስ ብቅል የጀርመንን የቢራ ጠመቃ መስፈርትን በማሟላት የሚጠመቅ ቢራ ነው፡፡
ፋብሪካው 200 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ፈሰስ በማድረግ በዓለም በቢራ ጠመቃ ቴክኖሎጂ ቁጥር አንድ የተባለለት ፋብሪካ በደብረብርሃን ከተማ የገነባ ሲሆን በጎንደር የሚገኘውን ነባሩን ፋብሪካውን ደግሞ በማስፋፋትና አቅሙን በማዘመን ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ ከጥር አጋማሽ ጀምሮ ከቢራ ጣዕምና ይዘት መጓደል ጋር በተያዘ ከተለያዩ አካላት ቅሬታዎች የደረሱን በመሆኑ በአፋጣኝ ችግሩን በመለየት እርምጃ ለመውሰድ የተንቀሳቀስን ሲሆን የደረሱን ቅሬዎችም ከተለመደው የቢራ ጣዕምና ይዘት መጓደል ጋር የተያያዙ እንጂ በሰው ጤና ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሊያመጣ የሚችል አልነበረም፡፡
የቢራ ጣዕምና ይዘት መጓደል አጋጣማቸው የተባሉ ምርቶች ጀርመን ሀገር በርሊን ወደሚገኘው VLB የሚባል ዓለም ዓቀፍ የቢራ ጠመቃ ምርምርና ጥናት ማዕከል በመላክ የናሙና ምርመራ አድርገናል፡፡ በውጤቱም ምንም አይነት ለሰውልጅ የጤና ጉዳት የማያሰከትል ምርት መሆኑን አረጋግጠናል፡፡ ይህም በኢትዩጵያ የምግብ የመዳኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባላስልጣን በድጋሚ የተረጋገጠ ሆኗል፡፡

በተቋማችንም ባደረግነው ማጣራት ከፋብሪካችን ምርት ውስጥ የቢራ ጣዕምዕና ይዘት መጓደል ደርሶባቸዋል ተብለው የተለዩት ምርቶቻችን አልፎ አልፎ የተከሰቱ እና 0.05% የማይበልጥ ድርሻ ያላቸው ብቻ መሆናቸውን አረጋግጠናል፡፡ምርታችን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚሰራጭ እንደመሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በመላው ሀገሪቱ ያሉ እና የቢራ ጣዕምና ይዘት መጓደል ያለባቸውን ምርቶች በመሰብሰብ ላይ እንገኛለን፡፡
የፋብሪካችን የቢራ ጠመቃ ባለሙያዎች ከተለያዩ አለማቀፍ የቢራ ጠመቃ ጥራት መቆጣጠሪያ መሳሪያ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ችግሮችን መርምረው በመድረስ ማስተካከያ እንዲደረግበት ሆኗል፡፡ በተጨማሪም ችግሩ ዳግም እንዳይፈጠር ተጨማሪ የጥራት ቁጥጥር ስርዓት ዘርግተን በመስራት ላይ የምንገኝ ሲሆን ከኢትዩጵያ የምግብ የመድኃኒት እና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ዳግም ናሙና በመውሰድ እና ገለልተኛ ምርመራ በማድረግ ቢራው የጥረት ደረጃው የጠበቀና ለደንበኛ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
ስለሆነም በዚህ አጋጣሚ የቢራ ጣዕምና ይዘት መጓደል ያለበት ምርት ላጋጠማችሁ ደንበኞቻችን በሙሉ ከልብ የመነጨ ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ በኋላ ፋብሪካችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ በጥራት ላይ ፈጽሞ የማይደራደር መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
© TIRET

No comments:

Post a Comment