የማይክሮሶፍት ኩባንያ መስራችና ባለቤት የሆኑት ቢልጌት ከምስረታ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሙንና ሚናዉን ከፍ አድርገዉ ካስቀመጡት የማይክሮሶፍት ኩባንያ የቦርድ አባልነታቸዉም ተሰናብተዋል። የ65 ዓመቱ ባለሃብት እንደ ምክንያት ያነሱት ደግሞ ከዚህ በኋላ ሙሉ ትኩረቴን የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ማድረግ እፈልጋለሁ የሚል ነዉ፡፡
እስከዚህ ሰዓት ድረስ ለኩባንያዉ ስኬትና በቴክኖሎጂዉ ዘርፍ ለዓለም አበረክተዋለሁ ላሉት ዓላማቸዉ ጸንተዉ መቆየታቸዉን የገለጹት ቢል ጌት፣ ከዚህ በኋላ ደግሞ ከባለቤታቸዉ ጋር በመሰረቱት “ቢል ኤንድ ሚሊንዳ ጌትስ ፋዉንዴሽን” የበጎ አድራጎት ድርጅት ዉስጥ ሙሉ ጊዜያቸዉን ሰጥተዉ እንደሚሰሩ ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል AFP ተናግረዋል። በዋናነትም ለዓለም ህዝብ ስጋት የሆኑ በሽታዎችን መከላከልና የሰብአዊ ድጋፍ ማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥተዉ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
ቢል ጌት ከአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ በመቀጠል የዓለማችን ቁጥር ሁለት ባለሃብት ሲሆኑ በ2020 የወጡ መረጃዎች የተጣራ ሃብታቸዉ 100 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ያመለክታሉ፡፡
No comments:
Post a Comment