Wednesday, March 11, 2015

ከታሪክ ማህደር …..

             

   
    አጤ ቴዎድሮስ /1845 - 1860 . / 15 አመት ያህል ኢትዮጵያን ካስተዳደሩ በኋላ ከእንግሊዞች ጋር በተፈጠረው ግጭት እጄን ለጠላት አልሰጥም በማለት 1860 . በራሳቸው ሽጉጥ ህይወታቸውን ሰውተዋል፡፡ አጤ ቴዎድሮስ በመቅደላ አምባ ራሳቸውን ከገደሉ በኋላ ደጃዝማች ካሳ ምርጫ /በዝብዝ ካሳ/ በትግራይ ዋግሹም ጎበዜ በላስታ ንጉስ ምኒልክ በሸዋ፣ በጎጃም ራስ ደስታ፣ በወልቃይት ጥሶ ጎበዜ ሆነው የንጉሰ ነገስትነቱን ስልጣን ለማግኘት ወታደር እያስታጠቁ ጦር እየሰበቁ በመሽቀዳደም ላይ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ዋግሹም ጎበዜ ኃይላቸውን ይበልጥ አጠናክረው በጌምድር፣ ጎጃም እና ወሎንም ካሰገበሩ በኋላ ስመ መንግስታቸውተክለ ጊዮርጊስተብሎ በጎንደር 3 አመት ያህል ነገሱ፡፡

   ምንም እንኳ የጎጃም፣የወሎ እና የበጌምድር ገዥዎች አሜን ብለው ቢቀበሉም የትግሬ መሸፈት ስላሰጋቸው የወታደራቸውን ብዛት ለማሳወቅ አንድ ስልቻ ጤፍ ሞልተው ለበዝብዝ ካሳ ይልካሉ፡፡ በዝብዝ ካሳ /ካሳ ምርጫ/ የአጤ ተክለ ጊዮርጊስ አባት አንካሳ መሆናቸውን በማስታወስከቱርክ ይዋጋል እንኳን ካንካሳ ያባ ፈንቅል ልጅ ወሬሳው ካሳብለው ፎክረውወታደርህ ቢበዛ በጥይት ነው የምቆላውበማለት ጤፉን አስቆልተው ላኩላቸው፡፡  

  በዚህኑ ጊዜ የአጤ ተክለ ጊዮርጊስ ባለቤት የደጃዝማች በዝብዝ ካሳ እህት እቴጌ ድንቅነሽ እንዲህ ብለው ገጠሙ -

"ተዉ እናንተ ሰዎች ወደ አድዋ አትሂዱ
በእሳተ ገሞራ እንዳትነዱ
ያባ በዝብዝ ካሳ ቆራጥ ናትና ሆዱ"፡፡
ከዚያ በኃላ አደዋ ላይ ሐምሌ 5 ቀን 1863 .. ጦርነት ተጋጥመው አጤ ተክለ ጊዮርጊስ ተማረኩ፡፡ በአምባ ሰላማ ተራራ በእስራት እንዲቆዩ በተደረገበት ጊዜም እቴጌይቱ የሚከተለውን ገጠሙ -


  "ተናግሬ ነበር እኔስ አስቀድሜ
አሁን ምን ልናገር ከሀዘን ላይ ቆሜ
የተሻረው ባሌ ተሿሚው ወንድሜ
ከእንግዲህስ ወዲህ አለምንም ዕድሜ"፡፡

  
ደጃዝማች ካሳ ለበዓለ ንግሳቸው ሲዘጋጁ ከቆዩ በኋላ ጥር 13 ቀን 1864 .. “ዮሐንስ አራተኛ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያተብለው በአቡነ አትናቴዎስ እጅ በአክሱም ጽዮን ስርአተ ንግስናቸው ተፈፀመ፡፡

  ግብፆች የአባይ ወንዝ ዋናው ምንጩ ከኢትዮጵያ ስለሆነና ይህም ወንዝ ለግብፆች የህይወታቸው ምሰሶ በመሆኑ፣ ግብፅ እና ኢትዮጵያ ከፈረዖኖች ዘመነ መንግስት ጀምሮ በየጊዜው እየተዋጉ መኖራቸውን ታሪክ ይመሰክራል፡፡ 

  አጤ ዮሐንስ የቱርኮች እና የግብፆች የተባበረ ጦርን ጉንዲት ላይ ህዳር 7 ቀን 1867 .. እና ጉራዕ ላይ የካቲት 30 ቀን 1868 .. ድል አድርገዋቸዋል፡፡


    አጤ ዮሐንስም ከድል በኃላ ለምርኮኞቹ ምህረት በማድረግ ከባህር ማዶ አሻግረው ሲያባርሩየግብፅ ሰራዊት በጫማው እና በእግሩ የሀገሬን አፈር ይዞብኝ እንዳይሄድ ጫማውን አስወልቃችሁ ፣እግሩንም አጥባችሁ ባህሩን አሻግራችሁ አባሩትብለው ለሰራዊታቸው ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ድርሳናት ይጠቁማሉ፡፡

    
    እዚህ ላይ ቀደምት ነገስታት እና አባቶች ለሀገራቸው እና ለአፈራቸው ያላቸውን ፍቅር በእንዲህ እና በእንዲያ አይነት ነበር የሚገልጡት፤ አሁንስ ሲባል…... መልሱን ለእናንተ ትቻለሁ፡፡ ለማንኛውም እናንተም የምታወቁትን ያነበባችሁትን አካፍሉኝ፡፡

No comments:

Post a Comment