Friday, March 13, 2015

የቅማንት ማህበረሰብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

     

   የአማራ ክልል ምክር ቤት በቅማንት ማህበረሰብ የራስን በራስ አስተዳደር ጥያቄ ውሳኔ ሀሳብ ላይ ከተወያየ በኋላ ተገቢነቱን ተቀብሎ በአብላጫ ድምጽ አፀደቀ፡፡ የህግ፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብበሳቢ አቶ አርአያ ስላሴ ዓለሙ እንዳሉት የቅማንት ማህበረሰብ የራስን በራስ አስተዳደር ጥያቄ የውሳኔ ሃሳብ /ሞሽን/ ለክልሉ ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤ በማቅረብ የምክር ቤት አባላት በውሳኔ ሀሳቡ ላይ በስፋት ተወያይተዋል፡፡
 

   በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋና በላይ አርማጭሆ ወረዳ የቅማንት ማህበረሰብ በስፋት ይኖርባቸዋል ተብለው በጥናት በተለዩ 42 ኩታ-ገጠም ቀበሌዎች ራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ምክር ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ውሳኔው የተላለፈው በ23 ድምፀ ተአቅቦ፣ በሁለት ተቃውሞና በ189 ድጋፍ ማህበረሰቡ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር በአብላጫ ድምፅ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ጉባኤው አፅድቆታል፡፡


   ማህበረሰቡ አስተዳደር በማዋቀር ከመጭው በጀት ዓመት ጀምሮ በራሱ በጀትና የራሱን የሰው ኃይል በማደራጀት ራሱን በራሱ ማስተዳደር እንደሚጀምር አቶ አርአያ ስላሴ ዓለሙ አስታውቀዋል፡፡ የሚዋቀረው አስተዳደር በወረዳ ወይስ በምን ደረጃ እንደሚሆን ወደፊት በሚወጡ ህጎች በምክር ቤቱ የሚወሰን እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡
                                                  ምንጭ፡- ኢዜአ 

No comments:

Post a Comment