ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ የካቲት 25 ቀን 1938 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ከደራሲ አባታቸው ገሪማ ታፈረና ከመምህርት እናታቸው ተወለዱ፡፡ በአሁኑ ወቅት ኑሯቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ ልክ ዛሬ የካቲት 25 ቀን 2012 ዓ.ም 74ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡
ጤዛ የተሰኘውን ፊልም በአማርኛ በመስራት ብቃታቸውን በኢትዮጵያውያን የፊልም ታዳሚዎች ዘንድ ያስመሰከሩት ፕሮፌሰሩ በአለም ዓቀፍ ደረጃም እውቅና ያገኙባቸውን በርካታ ፊልሞች ሰርተዋል፡፡ በ1960ዎቹና በ1970ዎቹ በኢትዮጵያ የነበረውን ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ሁኔታ ማራኪ በሆነ አቀራረብ ባሳዩበት ጤዛ ፊልም በጎንደርና በአዲስ አበባ ከተሞች እንዲሁም በጀርመን ሀገር የኢትዮጵያውያንን አኗኗር ፍንትው አድርገው አሳይተዋል፡፡
ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ በጤዛ ፊልም በአማርኛ ፊልሞች ላይ ተሞክረው የማያውቁ የፊልም አሰራር ቴክኒኮችን በመጠቀም እና ፊልም እንኳን ተውነው ተመልክተው የማያውቁ ተዋናዮችን በማሳተፍ አስደናቂ የፊልም ዳይሬክቲንግ ብቃታቸውን አሳይተዋል። በጎርሳውያኑ አቆጣጠር ከ1975 ጀምሮ በሀዋርድ ዩኒቨርስቲ የፊልም አሰራር ጥበብ መምህር ሲሆኑ በጎርሳውያኑ 1993 በሰሩት ሳንኮፋ ፊልም ከፍተኛ አለማቀፍ እውቅናና ተቀባይነትን አግኝተዋል፡፡
ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ የሰሯቸው የፊልም ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፡-
1972 – Hour Glass Hour Glass
1972 – Child of Resistance
1976 – Bush Mama
1976 – Mirt Sost Shi Amit (also known as Harvest: 3,000 Years)
1978 – Wilmington 10 — U.S.A. 10,000
1982 – Ashes and Embers
1985 – After Winter: Sterling Brown
1993 – Sankofa
1994 – Imperfect Journey
1999 – Adwa – An African Victory
2009 – Teza
ዛሬ (የካቲት 25) የኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ፊልም ሰሪ እና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ የልደት ቀን ነው ፤ በመሆኑም መልካም ልደትን ተመኝተናል፡፡
No comments:
Post a Comment