Sunday, June 29, 2014

የኮምቦልቻ ኤርፖርት አገልግሎት መስጠት ሊጀምር ነው


  በአማራ ክልል ኮምቦልቻ  እየተገነባ ያለው ኤርፖርት ከሁለት ወር በኃላ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት አስታወቀ። የድርጅቱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ወንድም ተክሉ እንደገለጹት ኤርፖርቱ በአሁኑ ጊዜ በአስፓልት ደረጃ ተጠናቋል።

 ኤርፖርቱ 150 ሚሊዮን ብር ተመድቦለት ላለፉት 3 አመታት ግንባታው ሲካሄድ ቆይቷል። የኤርፖርቱ ስራ መጀመርም በአገሪቷ ያሉትን ኤርፖርቶች ቁጥር ወደ 18 ያሳድገዋል። የኮምቦልቻ ኤርፖርት ትልልቅ አውሮፕላኖችን የማሳረፍ አቅም እንዳለው ሃላፊውን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባቸውን 22ሺ 497 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን አስመርቀ፡፡

   እሁድ ሰኔ 22፣2006 ከተመረቁት ቤቶች መካከል 11 ሺ ያህሉ እጣ የወጣባቸው፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ለነዋሪዎች ያልተላለፉ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶች ናቸው። 

   በምረቃው ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮነን መንግስት በከተሞች ያለውን የቤት ችግር ለመቅረፍ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

  የቤት ልማት ምርሃ ግብሩ ከተማዋን ደረጃ የጠበቀች ከማድረግ ባሻገር ለድህነት ቅነሳውና  ለቁጠባ መሰረት እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡

  የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በበኩላቸው አስተዳደሩ ለተጠቃሚዎች ያስተላለፋቸው ቤቶች መሰረተ ልማት የተሟላላቸው ናቸው ብለዋል፡፡ ከንቲባው እንዳሉት በሚቀጥሉት 3 ወራትም 73ሺ ቤቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ይደረጋሉ፡፡አስተዳደሩ የከተማዋን የቤት ችግር ለመቅረፍ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡


  ከምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ቁልፍ የተረከቡ እድለኞች  መንግስት የከተማዋን ህዝብ የቤት ባለቤት እያደረገ ያለውን ጥረት እንዲያጠናከር ጠይቀዋል፡፡የጋራ መኖሪያ ቤቱን ለማግኘት አጋጣሚው የቁጠባ ባህላቸውን እንዳሳደገላቸውም ለኢሬቴድ ተናግረዋል፡፡

 በቤቶቹ ግንባታ ላይ 785 የስራ ተቋራጮችና 939 ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ተሳትፈውበታል፡፡ ከተመረቁት የጋራ መኖሪያ ቤቶች በየካ 9 ሺ 766፣ በአቃቂ ቃሊቲ 5 ሺ 310፣ በቂርቆስ 1 ሺ 536 እና በጉለሌ ክፍለ ከተማ ደግሞ 5 ሺ 885  ናቸው ።

Friday, June 27, 2014

አዲስ አበባ በከተማ ልማት በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት 3ኛ ሆነች



  በከተማ ልማት ከዓለማችን በማደግ ላይ ካሉ አገራት ውስጥ አዲስ አበባ 3 በመሆን ተመረጠች ።ኤቴ ኬርኒይ የተባለ ድረ ገፅ በከተማ ልማት በፍጥነት እያደጉ ካሉ አገሮች አዲስ አበባን በሶሰተኛነት ደረጃ አስቀምጣቷል።  ድረ ገፁ እንዳለው ከኢንዶኔዥያዋ ጃካርታ እና ከፊሊፒንሷ ማኒላ ከተማ ቀጥሎ በከተማ ልማት በፍጥነት እያደጉ ያሉ አገሮች ሲል አዲስ አበባን በሶሰተኛነት አስቀምጣቷል። ደረጃውን ያወጣው ኤቴ ኬርኒይ የተባለ የአሜሪካን ድረ ገፅ ሪፖርት እንዳለው 34 የሚሆኑ በዝቅተኛ እና በመካከለኛ ገቢ በፍጥነት እያደጉ ያሉ አገራትን ለውድድር አቅርቧል።

  ፍትሐዊ የሃብት ክፍፍል፣ የአካባቢ ጥበቃና የከተማ መሰረተ ልማት በከተማው ያለው የፖለቲካ መረጋጋት በሚል በሁሉም መስፈርት አወዳድሮ ከፊሊፒንስ በመቀጠል አዲስ አበባን 3 ደረጃ ሰጥቷታል። በተጨማሪም በንግድ እንቅስቃሴ፣በሰራተኞች ደህንነትና ጥበቃ ከመስፈርቶቹ መካካል የሚጠቀሱ ናቸው። በደረጃው አንደኛ ጃካርታ፣ ሁለተኛ ማኒላ ሶስተኛ ደግሞ አዲስ አበባ ሆነዋል።

  በተመሳሳይ በመላው ዓለም በኢኮኖሚ ከበለፀጉ 40 አገሮች ወስጥ በከተማ ልማት ደረጃም ይፋ ተደርጓል፡፡ኒዮርክ ከተማ በአንደኛነት ስትቀመጥ የእንግሊዟ ለንደን በሁለተኝነት የፈረንሳዩዋ ፓሪስ ከተማ ደግሞ የሶስተኝነት ደረጃን አግኝታለች።

ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን በዓለም አቀፍና በአገር ውስጥ የጥራት ተሸላሚ ሆነ


 
   በኒውዮርክ-አሜሪካ በተደረገውዓለም አቀፍ ኳሊቲ ሰሚትየጥራት ተሸላሚ የሆነው ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን፤ በአገር ውስጥም የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ድርጅት 3 ዙር የጥራት ውድድር አንደኛ ደረጃ የክብር ሽልማት ማግኘቱን ገለጸ፡፡ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፉ አምባዬ ሽልማቱን አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ግንቦት 16 ቀን 2006 በኒውዮርክ ማሪዮት ማርኪዝ ሆቴል በቢዝነስ ኢኒሸቲቭ ዳይሬክሽንስ (ቢአይዲ) በተደረገው 28ኛው የጥራት ውድድር፣ የተክለብርሃን አምባዬ ኪንስትራክሽን እናት ኩባንያ የሆነውታፍ ኮሮፖሬት ግሩፕ118 አገሮች ከተውጣጡ ታዋቂ ኩባንያዎች ጋር ተወዳድሮ የጥራት ተሸላሚ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ አሁን በዓለም አቀፍና በአገር አቀፍ ደረጃ የተሰጡን የጥራት ሽልማቶች፣ ኢትዮጵያ በመላው ዓለም በጥራት መወዳደር የሚችሉ ድርጅቶች እያፈራች መሆኑን አመልካች ነው ያሉት አቶ ሰይፉ፤ ሽልማቶቹ፤ መላው ሰራተኛና አመራሩ፣ ጥራትን መሰረት ያደረገ ሙያዊ የአሰራር ሥነ-ምግባር በድርጅቱ ውስጥ በመዘርጋትና በመተባበር የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል፡፡

   የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ድርጅት በቅርቡ 3 ጊዜ በሸራተን ሆቴል ባደረገው የጥራት ውድድር፤ ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን አንደኛ ደረጃ የማዕረግ ተሸላሚ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል፡፡ በአገር ውስጥ የጥራት ተሸላሚ መሆን የቻሉበትን ምክንያት ሲገልጹም፤ከአሁን በፊት የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ድርጅት ባዘጋጀው ውድድር ተሳትፈን ነበር፤ ልንሸልም ቀርቶ የምስክር ወረቀት እንኳን አልተሰጠንም፡፡ ለምንድነው ያልተሸለምነው? ብለን ጠየቅን፡፡የቀረቡትን የመወዳደሪያ መለኪያ መስፈርቶች ስላላሟላችሁ ነውተባልን፡፡ በተነገረን መሰረት ጉድለቶቻችንን አርመንና አሟልተን እንደገና በመወዳደር፣ ይኼው ለሽልማት በቃን ብለዋል፡፡21 ዓመት በፊት 1985 . ኢንጂነር ተክለብርሃን አምባዬ 5,000 ብር ካፒታልና ከሁለት የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ያቋቋሙት ደርጅት፤ ዛሬ 850 ቋሚና 200 ጊዜያዊ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን በዓመት 800 ሚሊዮን ብር በላይ ሥራዎችን ያከናውናል፡፡ ሥራ አስፈጻሚው የስኬታቸው ምስጢር፣ ሰራተኞቻቸውን በአግባቡ መያዛቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ብዙ ድርጅቶች ያልተለወጡት ሰራተኛው አልምጥ ስለሆነ፣ ሥራ ስለማይወድ እንደሆነ ይገልፃሉ ያሉት አቶ ሰይፉ፤ እውነቱ ግን አይደለም ይላሉ፡፡ችግሩ ሰራተኞቻቸውን ስላላቀረቧቸውና የሥራው ባለቤት ስላላደረጓቸው ነው፡፡
 
   እኛ ግን ሰራተኞቻችን መተኪያ የሌላቸው ሀብታችን ናቸው፡፡ አንድ ሰራተኛ ሲያጠፋ አናባርረውም፡፡ችግርህ ምንድነው?› ብለን እናወያየዋለን፤ ብዙ ጊዜ የሰራተኛው ችግር የሙያና የእውቀት ማነስ እንጂ 99 ከመቶ ያህሉ ቅንና ሥራ ወዳድ ነው፡፡ሲሉ አስረድተዋል፡፡ ይሄን የሙያና የእውቀት ጉድለት ለማሟላትም ለስልጠና በዓመት 2. ብር እናወጣለን ብለዋል፡፡ሰራተኛው የሥራው ባለቤት እንዲሆን ኃላፊነትና የመወሰን ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ከማኔጅመንቱ ጋር ከዕቅድ ጀምሮ ይሳተፋል፡፡ ያልመሰለውን ነገር አይቀበልም፡፡ እንዲህ ሲደረግ ውጤቱ እንዲህ ይሆናል በማለት ይቃወማል፡፡ ታዲያ ሰራተኛው አምኖ ያፀደቀው እቅድ እንዴት ውጤታማ አይሆንም?...” በማለት ተናግረዋል፡፡ ተክለብርሃን አምባዬ ኮንስትራክሽን፤ በአሁኑ ወቅት ከአገር ውስጥ አልፎ በአፍሪካ አገራትም መስራት የጀመረ ሲሆን በሱማሌ ላንድ የአውሮፕላን ማረፊያ እየገነባ ነው፡፡ በዩጋንዳም በቤቶች ግንባታ ለመሰማራት በእንቅስቃሴ ላይ ነው ብለዋል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፡፡
                                                          ምንጭ ፡- ሪፖርተር