የ27 ዓመቷ ሱዳናዊት የስምንት ወር ነፍሰጡር ስትሆን ሃይማኖቷን ከሙስሊም ወደ ክርስትና በመቀየሯ የሞት ቅጣት
ፍርድ ተላልፎባታል፡፡ ማሪያም ያህያ የተባለችው ይህችው ወጣት ሃይማኖቷን መልሳ ወደ እስልምና እንድትቀይር የሶስት
ቀን የግዜ ገደብ ተሰጥቷት የነበረ ቢሆንም ይህን ባለማድረጓ የሞት ፍርዱ እንዲጸናባት ተደርጓል፡፡
ፍርደኛዋ በአባቷ ሱዳናዊ እና ሙሰሊም መሆኗ የተገለጸ ሲሆን እናቷ ደግሞ ኢትዮያዊ ዜግነት ያላት የኦርቶዶክስ ክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ነች ተብሏል፡፡ በልጅነት እድሜዋ አባቷ ከእርሷ ጋር ባለማሰለፉ እና የእስልምናን ትምህርት ባለመማሯ ሃይማኖቷን መቀየሯ ተጠቅሷል፡፡
ፍርዱን በመቃወም 50 የሚያህሉ ሰዎች ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸው የተገለጸ ሲሆን አምነስቲ ኢንተርናሽልም በጉዳዩ ላይ ተቃውሞውን አሰምቷል፡፡አንዳንድ የዜና አውታሮች የኢትዮጲያ መንግስት ጣልቃ መግባት አለበት ሲሉም ተሰምተዋል።

No comments:
Post a Comment