Monday, May 26, 2014

በ2014ቱ የአለም የዱላ ቅብብል ውድድር ኢትዮጵያ በወንዶች 4 በ1500 ሜትር ሶስተኛ ሆና አጠናቀቀች


   በባሃማሷ ናሱ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የአለም የዱላ ቅብብል የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያ በወንዶች 4 በ1500 ሜትር በሶስተኝነት አጠናቀቀች። የኬንያ አትሌቶች በ14 ደቂቃ ከ22.22 ሰከንድ  የአለም ሪከርድን በሰበሩበት በዚህ ውድድር ፤ አሜሪካውያን የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ሁለተኛ በመሆን ጨርሰዋል።

 ብርቱ ፉክክር ያደረጉት ኢትዮጵያውያኑም ውድድሩን በ14 ደቂቃ ከ41.22 ሰከንድ በማጠናቀቅ የሀገራቸውን ሪከርድ ማሻሻል ችለዋል። በዚህ ውድድር ጃማይካውያን በወንዶች 4 በ200 ሜትር እንዲሁም ኬንያውያን በሴቶች 4 በ 1500 ሜትር የዱላ ቅብብል አዲስ የአለም ክብረ ወሰን አስመዝግበዋል። በ4 በ100 እና በ4 በ400 ሜትር ውድድር ከ1ኛ እስከ 8ኛ ያጠናቀቁት አትሌቶች ፥ በ2015 ዓ.ም በቤጂንግ ለሚደረገው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በቀጥታ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

No comments:

Post a Comment