በፈጣን እድገት ላይ የሚገኘው እና የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአቭየሽን ማሰልጠኛ አካዳሚ ነው በአፍሪካ የአየር መንገዶች መሀበር የ2014 ‹‹ምርጥ የአየር መንገድ አገልግሎት ስልጠና ሰጪ›› ተብሎ የተመረጠው፡፡
አየር መንገዱ ናይሮቢ በተካሄደው አመታዊው የአቭየሽን አቅርቦት እና ባለድርሻ አካላት ስብሰባ ላይ በተደረገ የሽልማት ስነ ስርአት ላይ ሽልማቱን በኢትዮጵያ የአቪየሽን አካዳሚ ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል አሰፋ አማካኝነት ተቀብሏል፡፡ውጤታማ የአቪየሽን አገልግሎት ስልጠና በመስጠት የሚታወቀው አካዳሚው ለሌሎች የአፍሪካ አየር መንገዶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚሰጠው የላቀ ስልጠና እና ድጋፍ ለሽልማት እንዳበቃው ተገልጿል፡፡
አካዳሚው በአመት አንድ ሺህ ሰልጣኖችን በአውሮፕላን ማብረር ፣ በአውሮፕላን ጥገና ፣ በደንበኞች አገልግሎት ፣ በፋይናንሻል እና ሽያጭ እንዲሁን በሌሎች ተያያዥ ሙያዎች ተቀብሎ በማሰልጠን ከአፍሪካ ትልቁ የአቪየሽን አካዳሚ ነው፡፡የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በሽልማቱ አየርር መንገዱ ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው እና ለእህት የአፍሪካ አየር መንገዶች የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
ምንጭ ፡- ድሬ ቲዩብ
No comments:
Post a Comment