በቅዱስ ላሊበላ ከተማ የሚገኘው ቤተ ጊዮርጊስ ውቅር ቤተ ክርስቲያን በዓለም ላይ ካሉ እጅግ አስደናቂ የተቀደሱ ሥፍራዎች ውስጥ ተካተተ፡በቅርቡ ሀፊንግተን ፖስት ባወጣው መረጃ መሠረት፣ በዓለም ላይ ካሉና የተመልካችን ቀልብ ገዝተው ከተገኙ 19 ቦታዎች ውስጥ ቤተ ጊዮርጊስ አንዱ ሆኗል፡፡ በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (800 ዓመታት በፊት) በአፄ ላሊበላ ከተሠሩት 12 ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱ የሆነው ቤተ ጊዮርጊስ፣ ከሌሎቹ በተለየ በተደጋጋሚ በጎብኚዎች ፎቶግራፍ የተነሳ ሲሆን፣ የበርካታ ቱሪስቶች መዳረሻ በመሆን ከተቀሩት አብያተ ክርስቲያኖች የበለጠ ዝናን የተቀዳጀ ነው፡፡
ከመሬት ወደታች ዝቅ ብሎ የተገነባው ቤተ ጊዮርጊስ በጎብኚዎች ከሚያስወድዱትና ልዩ ከሚያደርጉት አንዱ 15 ጫማ ከፍታ ያለው የፀሐይ ግብዓት የሚታይበት ቦታ መሆኑ ነው፡፡በአጠቃላይ ኢየሩሳሌምን ተምሳሌት በማድረግ ቅዱስ ላሊበላ ከተማ ላይ የተገነቡት 12ቱ አብያተ ክርስቲያናት እ.ኤ.አ. በ1978 ዩኔስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት የመዘገባቸው ሲሆን፣ በወቅቱ ‹‹የኢትዮጵያ ክርስትና መገለጫና ዛሬም ድረስ የፅናት መገለጫ ሥፍራ›› በሚል ተገልጾ ነበር፡፡ ሀፊንግተን ፖስት ከመረጣቸው 19 መዳረሻዎች ውስጥ የፈረንሳዩ ሴንት ሚካኤል ዲጉይልሔ ቻፕል፣ ህንድ የሚገኘው አበባማ ቅርፅ ያለው ሎቱስ ቴምፕል ይገኙበታል፡፡
No comments:
Post a Comment