Wednesday, September 3, 2014

የዓለም ኃይማኖቶች የሠላም ጨዋታ ተካሄደ


  የዓለም ኃይማኖቶች ህብረት ለዓለም ሠላም በሚል ሃሳብ በጣሊያኗ ዋና ከተማ ሮም አንጋፋ የእግር ኳስ ተጫዋቾች በተሳተፉበት ተካሂዷል። የቀደመው እና የአሁኑ ዘመን የእግር ኳስ ባለታሪኮች በሁለት ቡድን ተከፍለው ያደረጉት ጨዋታ፣ ኃይማኖቶች ለዓለም ሠላም መስፈን የሚያደርጉትን ጥረት ያለልዩነት እንዲሰሩ ለማድረግ አልሟል። 

 

  በጨዋታው ላይ በየሀገራቱ ያሉ የተለያዩ ኃይማኖት ተከታይ ተጫዎቾች ሲካፈሉ የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል እና የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተከላካይ ደጉ ደበበ ተሳታፊ ሆኗል። ውድድሩን የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ጳጳስ ፍራንሲስ እና የቀድሞው የኢንተርሚላን ተከላካይ  ዣቪየር ዛኔቴ በጋራ አዘጋጅተውታል። በጨዋታው ውጤትም የዛኔቲ ቡድን በአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር የተመራውን የጳጳሱ ቡድን፣ 6 ለ 3 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

No comments:

Post a Comment