Tuesday, September 16, 2014

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ

   
በ1962 ዓ.ም የተመሰረተው የባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከአ.አ. በ4ዐዐ ኪ.ሜ ርቀት  በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ይገኛል፡፡ ስፋቱ ወደ 22ዐዐk.m2 የሚደርስ ሲሆን ከሰሜን ወደ ደቡብ 74 ኪ.ሜ ከምዕራብ ወደ ምስራቅ ደግሞ 53 ኪ.ሜትር ይሰፋል፡፡ ፓርኩ ከባህር ወለል በላይ ከ145ዐ እስከ 4377 ጫማ ባለ ልዩነት ውስጥ የሚገኙ አካባቢዎችን ያካትታል፡፡ 4377 ጫማ የሚረዝመው እና ከኢትዮጵያ በከፍታው ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የቱሊ ዲምቱ ተራራን ጨምሮ የአፍሮ አልፓይን ከፍተኛ ቦታዎች በዚህ ፓርክ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የባሌ ተራሮች ከፍተኛ አካባቢ በተለያዩ መንገድ የተፈጠሩ ሀይቆች፤ እርጥበት አዘል መሬቶች፣ የእሳተጎሞራ ቅሪቶችን አቅፎ ይዟል፡፡
  ፓርኩን ልዩ የሚያደርገው ሌላው ነገር በኢትዮጵያ ትልቁና ወደ ሰባት ሺሕ ኪሎ ሜትር ስኩዬር የሚሸፍነው ‹‹የሐረና ደን›› በውስጡ በመገኘቱ ነው፡፡  ከነዚህም ውስጥ አንድ ሺሕ ኪሎ ሜትር ስኩዬር የሆነው በብሔራዊ ፓርኩ ውስጥ ሲገኝ የተቀረው ስድስት ሺሕ ኪሎ ሜትር ስኩዬር ድርሻ በኦሮሚያ ክልል የደንና ዱር እንስሳት ኢንተርፕራይዝ ይተዳደራል፡፡ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት ጊዜያዊ መዝገብ ውስጥ ተካቷል፡፡
 ከ1600 በላይ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ዓይነት ዕፅዋቶች፣ 78 ዓይነት አጥቢ የዱር እንስሳትና ወደ 200 የሚጠጉ አእዋፋት በፓርኩ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል 32 ዓይነት ዕፅዋቶች፣ 31 የሚጠጉ ብርቅዬና ድንቅዬ  የዱር እንስሳትና ወደ ስድስት የሚጠጉ ዕፅዋት በብሔራዊ ፓርኩ ካልሆነ በስተቀር በሌላው ዓለም ፈጽሞ አይገኙም፡፡ 

  በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ክልል ውስጥ ከሚገኙ 78 የሚደርሱ አትቢ የዱር እንሰሳት  17 የሚሆኑት በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ብርቅዬ እንሰሳት ናቸው፡፡ 

ከዚህ ባሻገር ለሳይንስና ኢኮሎጂ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው በደረታቸው የሚሳቡ ልዩ ልዩ እንስሳትና መንቆረርቶችን ፓርኩ አቅፎ ይዟል፡፡ ቡናና በኢትዮጵያ ውስጥ ለባህል መድኃኒትነት የሚውሉ 40 ከመቶ  ዕፅዋቶችም ይገኙበታል፡፡ በእዋት እና በእንሰሳት ብዝሃ ህይወት መበልፀግ ደረጃ ፓርኩ ከአለም 34ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡እንደ ዓለም አቀፍ የወፎች ድርጅት ሪፖርት ከሆነ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የአፍሪካ አራተኛው ‹‹በርዲንግ ሳይት›› ተብሎ ተመዝግቧል፡፡


  የባሌ ብሄራዊ ፓርክ በ “Bird lite International” በአለም ከሚገኙ አስፈላጊ የአዕዋፍ መኖሪያ ቦታዎች ጎራ ተመድቧል፡፡ በፓርኩ ከ28ዐ በላይ የአዕዋፍ ዝርያዎች ሲኖሩ ሲሆን ሰባቱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው፡፡
በባሌ ብሄራዊ ፓርክ ዋቢ ሸበሌ፣ ዌብ፣ ዱማል፣ ያዶት እና ወልመል የተሰኙ ወንዞች ይፈሳሉ፡፡ በባሌ ብሄራዊ ፓርክ ከሚገኙ የዱር እንስሳት መካከል ቀይ ቀበሮ፣ኒያላ ፣ አጋዘን እና ሌሎችም ይጠቀሳሉ፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ ቀበሮ


ይህ ቀይ ቀበሮ አኗኗሩ በመንጋ ነው፡፡ አንድ መንጋ ከ3-13 አባላት ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ እያንዳንዱ መንጋ የራሱ የመኖሪያ አካባቢ ሲኖረው የአካባቢውን ድንበር ወንድ ቀይ ቀበሮዎች ያስከብራሉ፡፡ በርቢ ወቅት ሴት ቀይ ቀበሮ ከመንጋው አባላት ወንዶች ውጪ ግንኙነት ማድረግ አይፈቀድለትም፡፡ ከመንጋው አባላትም ጠንካራው ወንድ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ የተሻለ እድል አለው፡፡ የኢትዮጵያ ቀይ ቀበሮ ከማህበራዊ አኗኗራቸው ባሻገር በጠንካራ አዳኝነታቸው ጭምር ይታወቃሉ፡፡

ኒያላ /Mountain Nyalas/

   
ይህ የአጋዘን ዝርያ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ ብርቅዬ እንስሳ ነው፡፡ ቁመቱ 135 ሴ.ሜ በአማካኝ ይደርሳል፡፡ ሴቷ ኒያላ ከ15ዐ -- 2ዐዐ ኪ.ግ ወንዱ ደግሞ ከ18ዐ--3ዐዐ ኪ.ግ ይመዝናል፡፡ ኒያላ በባሌ ተራራማ አካባቢዎች ቁጥቋጦ፣ ሳር እና ዘርዘር ያለ የደን ሁኔታ በሚታይበት አካባቢ በስፋት ይኖራል፡፡ አንዲት ሴት ኒያላ ከ8-9 ወራት የሚቆይ የእርግዝና ጊዜ የሚኖራት ሲሆን በአንድ ጊዜ አንድ ትወልዳለች፡፡

  
የባሌ ብሄራዊ ፓርክ አስደናቂ የተራራ እይታዎች፣ ልዩ ስሜት የሚፈጥሩ ደኖች እና የውሃ አካላት ለቱሪስቶች ልዩ መስህብ ናቸው፡፡ በፓርኩ የሚገኙ የዱር እንስሳት እና አዕዋፍ ስብጥርም አስደናቂ ነው፡፡ ወደ ፓርኩ የሚጓዙ ቱሪስቶች የፓርኩን ተራራዎች በእግር በመውጣት /Trekking/ የማይረሳ ጊዜ ያሳልፋሉ፡፡በፓርኩ የሚገኙ የዳንካ፣ ዌብ እና ሻንያ ወንዞች እና ልዩ ልዩ የውሀ አካላት አሳ በማጥመድ ለሚዝናኑ ሀገር ጎብኝዎች የተለየ የእርካታ ምንጭ ናቸው፡፡ አሳ ለማጥመድ ግን ከፓርኩ አስተዳደር ፈቃድ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ 

10 comments:

  1. MakeMKV 1.14.3 Crack Plus Registration Code 2020 [Latest]


    MakeMKV Crack serves as a light-weight converter software which gives a straightforward tactic to transform a collection of Blu-Ray and DVD video clips into MKV format. It provides video conversion from various sorts of video files such as as Blu-Ray, DVD video, ISO, HD-DVD, or other files to MKV format. The program converts every single video clips from propriety disc to your set of MKV files. However, it provides a quality conversion chore and is not going to switch the initial information. You may enjoy your MKV files at varieties of platforms as it is supported by a great number of video players. Also, transform your other files into MKV structure.

    ReplyDelete
  2. This site have particular software articles which emits an impression of being a significant and significant for you individual, able software installation. This is the spot you can get helps for any software installation, usage and cracked"https://crackglobal.com"

    ReplyDelete
  3. Please let me know if you’re looking for an author for your weblog.
    You have some really good posts and I believe I would be a good asset.
    If you ever want to take some of the load off, I’d love to
    write some content for your blog in exchange for a link back to mine.
    Please send me an email if interested. Thanks!
    avg antivirus pro apk crack
    sony vegas pro crack
    avee music player apk cracked
    cubase pro crack

    ReplyDelete
  4. Thanks for sharing such great information, I highly appreciate your hard-working skills which are quite beneficial for me. eset-endpoint-security-crack

    ReplyDelete
  5. Thanks for this post, I really found this very helpful. And blog about best time to post on cuber law is very useful. ccleaner-professional-crack

    ReplyDelete
  6. But that doesn't mean action movie 2017 ​was a complete disappointment. Instead, the year has brought us many surprises of new voices in Asia. Of course, these weren't the only movies that impressed, as you are about to see. To wrap up another year, we'll look back at some of the best Asian titles released in 2017, as well as "older" titles we first discovered (or in some cases revisited!).
    https://showbizclan.com/best-asian-action-movies/

    ReplyDelete
  7. Such great and nice information about software. This site gonna help me a lot in finding and using much software. Kindly make this like of content and update us. Thanks for sharing us Toon Boom Storyboard Crack . Kindly click on here and visit our website and read more

    ReplyDelete
  8. Really Good Work Done By You...However, stopping by with great quality writing, it's hard to see any good blog today.
    PROcrackerr
    Free Xvideos Downloader CRACK

    ReplyDelete
  9. Really Good Work Done By You...However, stopping by with great quality writing, it's hard to see any good blog today.
    ProcrackerPC
    cracksoftwarefreedownload.com
    Anni Crack
    Yandex Browser CRACK

    ReplyDelete