Monday, March 3, 2014

የአሜሪካ መንግስት ስምንት ሽልማቶችን ለኢትዮጵያ ድርጅቶች ሰጠ

 የአሜሪካ መንግስት ስምንት  የሚሆኑ ሽልማቶችን በኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ልማት ገበያ ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች ሰጠ።ሽልማቱን ያዘጋጀው በአሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት የግብርና ልማት ፕሮግራም የቀንድ ከብት ልማት ፕሮጀክት ነው። 

   760 ሺህ  ዶላር  ሽልማት የተሰጣቸው እነዚህ ድርጅቶች በአገሪቱ የቀንድ ከብት ልማት ፈጠራና ኢንቨስትመንት  ረገድ የሚያበረታቱ ናቸው።ሽልማቶቹን  አዲስ ቀንድ ከብት ምርትና ምርታማነት ማሳደጊያ ተቋም፣እመቤትና ልጆቿ ወተትና የወተት አስተዋጽኦ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ኢትዮ ፊድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ፕሮጀክት ሜሪሲ፣የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም  አግኝተዋል።እንዲሁም ክፍያ ፋይናንሻል ቴክኖሎጂ ላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ዘማም ስንታየሁ ድርጅትና ሀርሜ ወተት እና የወተት ውጤቶች ላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ናቸው።

   
   ሽልማቱ  በቀንድ ከብት ልማትና ውጤቶች ዙሪያ ምርታማነትንና ተፎካካሪነትን ለማሳደግ ዓላማ አለው።አሜሪካ መንግስት አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዴኒስ ዌለር  በሽልማት ፕሮግራሙ  መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ድህነትንና የተዛባ የአመጋገብ ስርአትን በማቃለል ረገድ የኢትዮጵያ የቀንድ ከብት ልማት ዘርፍ ከፍተኛ አቅም አለው። 


   ሽልማቶቹ አገር በቀል ስራ  ፈጣሪዎችን የሚያነሳሱ ሲሆን፣ አዳዲስ ለገበያ  የሚሆኑ ምርቶች እንዲስፋፉ እንቅፋቶችን በማስወገድ ቀስ በ ቀስም የሥራ አድልን እንደሚያበረክት ይሆናልም ተናግረዋል ። የአሜሪካ መንግሰስት አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት የግብርና ልማት ፕሮግራም ቀንድ ከብት ልማት ፕሮጀክት በፊድ ዘ ፊውቸር መርሀ ግብር ለኢትዮጵያ መንግስት የግብርና ልማት ፕሮግራም እንደሚውል ኢዜአ የአሜሪካ ኤምባሲን ጠቅሶ ዘግቧል።

No comments:

Post a Comment