ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በሆቴል ዘርፍ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እያስመዘገቡ ከሚገኙ ከሰሀራ በታች ካሉ አምስት የአፍሪካ ሀገሮች ተርታ ተሰልፈዋል፡፡ ደብሊው ሆስፒታሊቲ የተሰኘ ድርጅት ደረጃቸውን ከጠበቁ አለማቀፍና አህጉር አቀፍ እንዲሁም ትናንሽ ሆቴሎች ላይ የዳሰሳ ጥናት ካካሄደ በኋላ ነው መረጃውን ይፋ ያደረገው፡፡
በቀጣይ በዘርፉ ኢትዮጵያን ጨምሮ ኡጋንዳ ፣ናይጄሪያ ፣አንጎላ እና ጋና ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍሰት እንደሚያገኙ ይጠበቃል ብሏል መረጃው፡፡ በተለይ ኢትዮጵያና ኡጋንዳ በዘርፉ ቁልፍ የኢንቨስትመንት መዳረሻ በመሆን ኬንያን መብለጣቸውንም ዘገባው አስቀምጧል፡፡
በያዝነው
ዓመት በዘርፉ በሚፈጠር የስራ እድልን ማዕከል በማድረግ በወጣው ደረጃ ፣ናይጄሪያ በሆቴል ኢንቨስትመንት ቀዳሚ
የኢንቨስተሮች መዳረሻ እንደምትሆን የተቀመጠ ሲሆን 53 ሺህ የስራ እድል በዘርፉ እንደሚፈጠር ተመላክቷል፡፡ በኢትዮጵያም 8 ሺህ 8 መቶ የስራ እድል እንደሚፈጠር ተጠቁሟል፡፡ ምንጭ፦ኒው ቪዥን
No comments:
Post a Comment