ደደቢት በ2005 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዋንጫ ባለቤት መሆኑን ተከትሎ ነው በዘንድሮው የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ እየተሳተፈ የሚገኘው። በመጀመሪያው ዙር ከዛንዚባሩ ኬ.ኤምኬ.ኤም ጋር ተደልድሎ በድምር ውጤት 3ለ2 አሸንፎ ለቀጣዩ ዙር ማለፍ በመቻሉ ነው ከቱኒዚያው ሴፋክሲያን ጋር እንዲገናኝ የተደረገው።
ደደቢት በዘንድሮ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያከናወነው 7ጨዋታዎችን ብቻ ሲሆን 6ቱ ተስተካካይ መርሃ ግብሮች ናቸው። ዛሬ እሁድ የካቲት 23 ቀን 2006 ከ10 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስቴዲዮም የሚደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የመግቢያ ዋጋ በተለመደው የሊግ ተመን መሆኑ ተገልጿል፡፡
በተያያዘ ዜና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በዚህ ሳምንት እጀመርዋለሁ ያለው ከ 17 አመት በታች የእግር ኳስ ውድድር አሁንም ቀኑ ተገፍቶ ወደ የካቲት 29 መራዘሙ የተሰማ ሲሆን የእድሜ ጉዳይ ሲያወዛግብ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ለውድድሩ መራዘም የቀረበው ምክንያት ማስረጃዎችን አጠናቀው ያላቀረቡ ክለቦች በመኖራቸው ነው፡፡ ካፍ ከአንድ ወር በፊት ነበር የውድድሩን መኖር ያሳወቀው፡፡ የተለያዩ መረጃዎች የሚያመላክቱት ኢትዮጵያ ከሲሼልስ ቡድን ጋር መደልደሏን እና ሚያዝያ ወር ላይም ግጥሚያቸውን እንደ ሚያደርጉም ነው።
ምንጭ ፡- ድሬ ቲዩብ ስፖርት

No comments:
Post a Comment