በሴኔጋል አስተናጋጅነት በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2015 ለሚካሄደው ከ20 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ የማጣሪያ ድልድል ወጥቷል። ባለፈው ሳምንት በደ.አፍሪካ ኬፕታውን በወጣው የእጣ ድልድል መሰረት የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን ከሲሸልስ አቻው ጋር ከሚያዚያ 4-6 ባሉት ቀናት ያደርጋል።
የመልስ ጨዋታቸውን ደግሞ አዲስ አበባ ላይ ከሚያዚያ 25-27 ይካሄዳሉ። የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን ጨምሮ አንጎላ ፣ ቤኒን ፣ ቡርኪናፋሶ ፣ ካሜሮን ፣ ግብፅ ፣ ጋና ፣ ሞሮኮ ፣ ማሊ ፣ ናይጄሪያ ፣ ጋቦን ፣ ዲ.ኮንጎ እና ዛንቢያ የመጀመሪያውን ዙር ያለማጣሪያ በቀጥታ ያለፉ ሀገሮች ናቸው።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን የመጀመሪያውን ዙር በደርሶ መልስ ሲሸልስን ካሸነፈ ቀጣዩ ተጋጣሚ የሚሆነው ደ. አፍሪካ ይሆናል። በሴኔጋሉ የአፍሪካ ዋንጫ ከ1ኛ-4ኛ የሚወጡ ሀገሮች አፍሪካን ወክለው 2015 በሚካሄደው የአለም ዋንጫ ውድድር ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ።
ምንጭ ፦ ኢትዮ ኪክኦፍ

No comments:
Post a Comment