Monday, May 27, 2013

    የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዋጋ ይፋ ሆነ

d     የ10 /90 እና የ20/ 80 የቤቶች ፕሮግራም ምዝገባን ለማካሄድ የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ ፡፡
ኤጀንሲዉ በነዚህ የቤት ፕሮግራሞች የመንግስት ሰራተኞች የተሻለ ጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ አመቻቻለሁ ብሏል፡፡4 ሺህ ሙያተኞችና የስራ ሃላፊዎች ምዝገባውን ለማካሄድ የሚያስችላቸውን ስልጠና  በመውሰድ ላይ መሆናቸውን ነው የገለፀው ፡፡

      የቤት ፈላጊዎች መመዝገብ የሚችሉት ካሉት የቤት ፕሮግራሞች በአንዱ ብቻ  በመሆኑ ከወዲሁ ወስነው እራሳቸውን እንዲያዘጋጁና ፥ ምዝገባው በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ብቻ የሚካሄድ በመሆኑ የቤት ፈላጊዎች በእድሉ  እንዲጠቀሙ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡ከሚፈልጉት የቤት መርሃ ግብር ፣ የቤት ዓይነትና  ዋጋ  ከወዲሁ ወስነው መዘጋጀት አለባቸው በማለት ከገንዛቤ ሊያስገቧቸው የሚችሏቸውን መነሻ  የቤቶች ዋጋን  ዝርዝር  ይፋ አድርጓል ።

  የ10/90 መርሃ ግብር አጠቃላይ የቤት ዋጋ 38ሺህ ብር

          የ20/80 መርሃ ግብር
ባለ አንድ መኝታ 126 ሺህ 721 ብር
ባለ 2 መኝታ 224 ሺህ ብር
ባለ 3 መኝታ 304 ሺህ 215ብር

        ለነባር 20/80
ስቱዲዮ 61 ሺህ ብር
የ40/60 መርሃ ግብር
ባለ 1 መኝታ 162ሺህ 645 ብር
ባለ 2 መኝታ 250 ሺህ ብር
ባለ 3 መኝታ 386 ሺህ 400ብር

     የማህበራት ቤት
ባለ 1 መኝታ 210 ሺህ ብር
ባለ 2 መኝታ 280 ሺህ ብር ፣ ባለ 3 መኝታ  385 ሺህ ብር
የ10/90 እና የ20/80 ቤቶች ምዝገባ  ከሰኔ  3 አስከ 21 2005  ዓመተ  ምህረት  ድረስ እንደሚካሄድ ኤጀንሲው ማስታወቁ ይታወሳል ።

Sunday, May 26, 2013


    ሌሊሳ ዴሲሳ ያደረገው የስፖርትን የሰላም ተምሳሌትነት የሚያሳይ ነው -ጆን ኬሪ

  የቦስተን ማራቶንን ያሸነፈው ሌሊሳ ዴሲሳ በቦስተን ማራቶን የተሸለመውን የወርቅ ሜዳሊያ በውድድሩ ማጠናቀቂያ ወቅት በደረሰው የቦንብ ጥቃት ለተጎዱ ዜጎች በማስታወሻነት አበርክቷል፡፡ አትሌቱ ዛሬ ግንቦት 18/2005 በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በመገኘት ለሃገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ሜዳሊያዉን አስረክቧል፡፡

    ጆን ኬሪ አትሌቱ ያበረከተው የማስታወሻ ስጦታ የስፖርትን የሰላም ተምሳሌትነት የሚያሳይ ነው በማለት አመስግነዋል።
       “እጅግ አስደንጋጭ ነበር። ይህንን በሰማሁ ጊዜ ደስታዬ ደብዝዟል” ያለው ሌሊሳ የቦስተን ህዝብ ለሱ ደስታ ያበረከተለትን ሜዳሊያ ለተጎጂዎች ለመስጠት መወሰኑን ገልጿል።

   የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ይህ ውጣት አትሌት አሁን እዚህ የተገኘው በቦስትን ማራቶን ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ያገኘውን ሜዳሊያ በማስታወሻነት ለመስጠት ነው። እንደዚህ አይነት ልዩ ክንዋኔ የሚፈፅሙ ደግሞ ጥቂቶች ናቸው፡፡ በወቅቱ በተከሰተው ድርጊት በማዘኑ የፈፀመው አርያነት ያለው ድርጊት እኔንም አስደምሞኛል፡፡ በጣም ላመሰግነው እወዳለሁ” ብለዋል። የቦስተንን ማራቶን ለሁለተኛ ጊዜ እንደሚያሸንፍም ተስፋ አድርጋለሁ ብሏል ።

Wednesday, May 15, 2013



ኮሚሽኑ የሙሰና ጥቆማ መስጫ አድራሻዎች ይፋ አደረገ

ኮሚሽኑ የሙሰና  ጥቆማ መስጫ አድራሻዎች ይፋ አደረገ
            ኢትዮጵያ ለተያያዘችው የጸረ ሙስና ትግል መጎልበት የህዝብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የፌደራል የስነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቋል፡፡ ኮሚሽኑ ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን በሙስና ተጠርጣሪዎች ላይ የወሰደውን እርምጃ በቀጣይነት ለማጠናከር   ህብረተሰቡ ለኮሚሽኑ የሚያደርሰው ጥቆማ በሚከተሉት አድራሻዎች ማቅረብ የሚችል መሆኑን ገልጿል፡፡
     በፋክስ ቁጥር 251-115-53 69 91
     በኢሜይል አድራሻ  feacinv@ethionet.et                         
     ከክፍያ ነጻ የጥቆማ ስልክ መስመር 988
            በተጨማሪም 251-115-52-77 81/74 /ቀጥታ/ ወይም 251-115-52-91-00 የውስጥ ቁጥር  232/222 የስልክ መስመሮችን በመጠቀም ጥቆማዎችን ማቅረብ ይቻላል። ጥቆማቸውን በአካል ለሚያቀርቡ አካላት ለገሃር በሚገኘው የኮሚሽኑ ቢሮ ቁጥር 214 ድረስ በመምጣት ጥቆማዎቻቸውን ማቅረብ ይችላሉ።

            የመኖሪያ ቤት ፈላጊዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ይፋ ተደረገ


     የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአራት ዓይነት የመኖርያ ቤቶች ግንባታ ፈላጊዎች የምዝገባ ጊዜ ይፋ አደረገ፡፡ አስተዳደሩ በተለይ በሦስት ፕሮግራሞች የመኖርያ ቤት ዋጋ ላይ ክለሳ አድርጓል፡፡

     የቤት ግንባታ ፕሮግራሞቹ 10/90፣ 20/80፣ 40/60 እና የመኖርያ ቤት የኅብረት ሥራ ማኅበራት ናቸው፡፡ 20/80 በመባል የሚጠራው የቤት ፕሮግራም ቀደም ሲል ሲካሄድ የቆየው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ፕሮግራም ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን በ1997 ዓ.ም. ከተመዘገቡት 453 ሺሕ ሰዎች መካከል መኖርያ ቤቱ ያልደረሳቸው ሰዎች በድጋሚ እንዲመዘገቡ ይደረጋል፡፡

      በዚህ የ20/80 ቤቶች ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን የሚፈልጉ ነዋሪዎች በየወረዳቸው ከሰኔ 3 ቀን 2005 ጀምሮ እስከ ሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ምዝገባው ይካሄዳል፡፡ ይህንን መኖርያ ቤት ለማግኘትም ነባር ተመዝጋቢዎች በድጋሚ ሲመዘገቡ ለባለሦስት መኝታ ቤት 685 ብር፣ ለባለሁለት መኝታ ቤት 561 ብር፣ ለባለአንድ መኝታ ቤት 274 ብር እና ለስቱዲዮ 151 ብር መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡  አዲስ ተመዝጋቢዎች የ20/80 ተመዝጋቢዎች ለባለሦስት መኝታ ቤት 489 ብር፣ ለባለ ሁለት መኝታ ቤት 401 ብር፣ ለባለ አንድ መኝታ ቤት 196 ብር መቆጠብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

    በገንዘብ መጠን ላይ ለውጡ የተደረገው ነባሮቹ የሚቆጥቡት ለአምስት ዓመት በመሆኑና አዲስ ተመዝጋቢዎቹ የሚቆጥቡት ለሰባት ዓመታት በመሆኑ ነው ሲሉ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ኃይለ ማርያም ገልጸዋል፡፡

    ለ10/90 ቤቶች ፕሮግራም እንዲሁ ምዝገባ የሚካሄደው ከሰኔ 3 እስከ ሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ነው፡፡ ይህ ፕሮግራም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የቀረበ ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለመሆን አንድ ቤት ፈላጊ 187 ብር በወር መቆጠብ ይጠበቅበታል፡፡ እዚህ ፕሮግራም ውስጥ ለመታቀፍ ተመዝጋቢው ድህነቱን የሚገልጹ ማስረጃዎችን ከተገቢው አካል ማቅረብ እንደሚጠበቅበት ተገልጿል፡፡

      ከእነዚህ ሁለት ፕሮግራሞች ውጪ ያሉት የመኖርያ ቤት ፕሮግራሞች ዝቅተኛ ወይም መካከለኛ ገቢ ያለውን የኅብረተሰብ ክፍል የሚመለከቱ አይደሉም፡፡ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ ባለፈው ዓርብ ግንቦት 2 ቀን 2005 ዓ.ም. በአስተዳደሩ ካቢኔ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንዳስረዱት፣ በ40/60 እና በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል የሚካሄዱት ፕሮግራሞች የተሻለ ገቢ ላለው የኅብረተሰብ ክፍል ነው፡፡

      የ40/60 ቤቶችን ተጠቃሚ ለመሆን ለባለአንድ ክፍል 857 ብር፣ ለባለሁለት መኝታ ቤት 1,337 ብር፣ ለባለሦስት መኝታ ቤት 2,133 ብር መቆጠብ የግድ ነው፡፡ በከተማው ውስጥ በመንግሥትና በግል ድርጅቶች ወይም በአነስተኛ ንግድ የተሰማራ ሰው፣ ከኑሮው ተርፎት ይህን ገንዘብ መቆጠብ እንደማይችል የብዙዎች እምነት ነው፡፡ ለመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበርም እንዲሁ በአዲሱ ደንብ መሠረት የሚጠየቀው ክፍያ መቶ በመቶ በመሆኑ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ከጨዋታ ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል እየተባለ ይነገራል፡፡

    በ40/60 ቤቶች ተጠቃሚ ለመሆን ከነሐሴ 5 ቀን እስከ ነሐሴ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ እንዲሁም የመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት ከሐምሌ 15 እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ምዝገባ ይካሄዳል፡፡

    ለመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ የሚደራጁ ሰዎች በኅብረት ሆነው አቅማቸውን አቀናጅተው የቤት ባለቤት የመሆን ፍላጎት ኖሮአቸው ነው፡፡ ነገር ግን መቶ በመቶ ክፍያ መጠየቁ ቤት የመሥራት ህልም የነበራቸውን ሰዎች እንዲደናቀፉ አያደርግም ወይ? የሚል ጥያቄ ከሪፖርተር የቀረበላቸው ከንቲባ ኩማ ሲመልሱ መሬት በሊዝ በጨረታ ወስደው፣ ከሪል ስቴት አልሚዎች ቤት በመግዛት ተጠቃሚ መሆን የሚችሉት የተሻለ ገቢ ያላቸው ነዋሪዎች ናቸው፡፡ በተጨማሪም 40/60 እና ማኅበራት አሁንም የተሻለ ገቢ ላላቸው የቀረቡ ናቸው ብለዋል፡፡

‹‹መጠየቅ ካለበት መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል እንደ አቅሙ አማራጭ ተሰጥቶታል ወይስ አልተሰጠም የሚለው ነው፡፡ በእኔ እምነት ዝቅተኛም ሆነ መካከለኛ ገቢ ላለው አማራጭ ተሰጥቶታል፡፡ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች የተያዙትን 10/90 እና 20/80 ቤት ልማት ፕሮግራሞች መንግሥት ይደጉማል፡፡ 40/60 እና ማኅበራትን ግን አቅሙ አለን እንችላለን የሚሉ ክፍሎች የሚገቡበት ነው፤›› ሲሉ ከንቲባ ኩማ ገልጸዋል፡፡

    ከንቲባ ኩማ በመግለጫቸው እንዳስረዱት፣ ሕገወጦችን ለመከታተል ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ኅብረተሰቡም ቤት እያላቸው በድጋሚ ለመመዝገብ የሚጥሩትን በንቃት እንዲከታተል ጠይቀው፣ ሆን ብሎ አቅዶ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት በሚመክር ማንኛውም ሰው ላይ ጠንከር ያለ ዕርምጃ እንደሚወሰድበት ከንቲባው አስጠንቅቀዋል፡፡

Monday, May 13, 2013



በአንድ ግለሰብ በተከፈተ ተኩስ 12 ሰዎች ተገደሉ


         በአንድ ግለሰብ በተከፈተ ተኩስ 12 ሰዎች ተገደሉ በባህር ዳር ከተማ ልዩ ስሙ አባይ ማዶ ወይም ቀበሌ 11 በተባለ ቦታ ትናንት ግንቦት 04/2005 ምሽት 2:45 ላይ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል ባልታወቀ ምክንያት በመነሳሳት ህብረተሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴውን በሚያደርግበት ወቅት በከፈተው የተኩስ እሩምታ 12 ሰዎችን ገድሏል፡፡
     ከሟቾቹ ዉስጥ ህጻናትሴቶችና አዛውንቶች  ይገኙበታል፡፡ በአደጋው የቆሰሉ ሌሎች ሁለት ግለሰቦችም ህክምና እየተደረገላቸው ነው፡፡ ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ ለማምለጥ ሲሞክር በፀጥታ ሃይሎች ክትትል ሲደረስበት ራሱን ወንዝ ውስጥ መወርወሩን  የአማራ ክልል ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ በጉዳዩ ላይ እያደረገ ያለውን ምርመራ እንዳጠናቀቀ ተጨማሪ መረጃ እንደሚሰጥ አስታውቋል::
    ይህ በእንዲህ  እንዳለ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ግድያውን አስነዋሪ የጭካኔ ተግባር ሲል አውግዞታል:: የሟቾች  የቀብር ስርዓትም በደብረ አባይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ተፈፅሟል፡፡ በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ  የተገኙት የአማራ  ክልል  ርእሰ መስተዳድር  አቶ አያሌው ጎበዜም የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል ።
    
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን  በበኩሉ በግለሰቡ ድርጊት ህይወታቸውን ባጡ ዜጎች  ህልፈተ ህይወት ምክንያት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል ፡፡በእንዲዚህ አይነቱ  ወንጀልም በህብረተሰቡና በፖሊስ መካከል ለአመታት የቆየው መልካም ግንኙነትም አይሻክርም ብሏል በመግለጫው  ፡፡ የፖሊስነት ሙያዊ ዲስፕሊን  በጎደላቸው መሰል ፖሊሶች ይህ አይነት ክስተት ደግም እንዳይፈጠር እንደሚሰራም ያለውን ቁጥርጠኝነት አረጋግጧል ፡፡

Minister Brehan Fired Moments After Progress Report to Parliament



   Prime Minister Hailemariam Desalegn has dismissed Brehan Hailu, minister of Justice, on Thursday, May 9, 2013, sources disclosed to Fortune. Berhan received a letter from the Prime Minister’s Office on Thursday informing the Minister that he had been removed from his position.Brehan had been serving in a ministerial capacity since 2005, when he was appointed by former Prime Minister Meles Zenawi as Minister of Information, which later on was dissolved by law. The decision by the Prime Minister to remove Brehan from office has not come as a surprise in government circles.
     Earlier he lost his position in the powerful Executive Committee of the ruling EPRDF, when elections were held in March 2013. He was under fire during the annual convention of his party, the Amhara National Democratic Movement (ANDM), held in Bahir Dar during the same month in prelude to the EPRDF congress. Both events were held in the same city this year.
    He was criticized by the bigwigs of the party for issues of incompetence when he was nominated to the central committee of ANDM by another member. Late last week, he was grilled by Asmelash W. Sellasie, chair of Parliament’s Legal & Administrative Standing Committee, for the Ministry’s sluggish conduct in completing the nation’s Penal Code, that had been under revision for many years. Brehan had appeared before Parliament on Thursday, reporting on the nine-month performance of his Ministry.

   Fortune’s repeated attempts to reach Brehan before going to press were unsuccessful. A representative of Debre Brehan, a small town 130Km north of Addis Abeba, Brehan has served in several positions at the regional state level. He was formerly an administrator for North Showa Zone in the Amhara Regional State, and then moved on to head of the Region’s Health Bureau, where he had joined the region’s cabinet at the time.
        Before being appointed by Meles Zenawi as the Minister of Information in 2005, he served as the head of the Ethiopian Radio & Television Agency. He was made a minister of Justice in 2008, where he served until last week. The Ministry will announce this new development on Jomo Kenyatta St. in the coming few days, according to senior officials of the Ministry that Fortune talked to.

    The announcement may also include the reappointment of Leul Kahssay as a state minister for Justice, according to officials at the Ministry who spoke on conditions of anonymity, as they are not authorized to speak to the media. Leul had been serving as a deputy minister of Justice under Brehan, before he was replaced in 2010. He has been floating with no formal appointment up until last week, according to a senior aide working in the Prime Minister’s Office.
                                                                               Source -  Addisfortune


የቤት ፈላጊዎች መስፈርትና የምዝገባ መመሪያ ይፋ ተደረገ


i       ግንቦት 3/2005  የአዲስ አበባ የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ የቤቶች አስተዳደር ኤጀንሲ  የ 40 በ 60 ፣ የ 10 በ90 እና 20 በ80 የጋራ መኖሪያ  ቤት ፈላጊዎች ማሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታና የምዝገባ ስነ ስርአት ይፋ አደረገ ፡፡
      በዚህም መሰረት የ 10 በ 90 እና የ 20 በ 80  ምዝገባ ከሰኔ 3 እስከ 21 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙት በሁሉም ወረዳዎች ይደረጋል ፡፡
      የ 40 በ 60 ምዝገባ ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  በተመረጡ ቅርንጫፎች  ከሀምሌ 5 እስከ 17  የሚካሄድ ሲሆን ፥ በማህበር ለሚደራጁ ደግሞ ምዝገባው  ከ ሀምሌ 15 እስከ 30 የሚካሄድ ይሆናል ፡፡
ለመንግስት ሰራተኞች ደግሞ በተለየ ሁኔታ  117 ኛ መመዝገቢያ ቦታ ተዘጋጅቶ ምዝገባው ለብቻ የሚካሄድ መሆኑን ቢሮው ጨምሮ አሳውቋል ፡፡
ለምዝገባ ብቁ ለመሆንም በቢሮው የሚከተሉት መስፈርቶች ተቀምጠዋል ፡፡
* እድሜው/ዋ ከ 18 አመት በላይ የሆነ
* በከተማው ውስጥ ቢያንስ ለሁለት ተከታታይ አመታት የኖረና እየኖረ ያለ።
* የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሆኖ ነገር ግን ለሁለት ተከታታይ አመታት በስራ ወይም በትምህርት ምክንያት ከከተማዋ ውጪ  የኖረበትን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና ፥ ማስረጃው ቦታውን ለምን ያክል ጊዜ እንደቆየ ወይም እንደሚቆይ በዝርዝር ካቀረበ ብቁ ይሆናል፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈግ የቁጠባ መጠን ደግሞ ይሄ ነው ብሏል ቢሮው ፥
ለ 40 በ 60
ለባለ 3 መኝታ ቤት  ብር 2453
ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 1275
ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር  1053
ለነባር 20 በ 80
ከምዝገባ ቀን ጀምሮ በየወሩ በተከታታይ 5 አመት መቆጠብ ይኖርበታል
ለ ባለ 3 መኝታ ቤት ብር 685
ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 561
ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር 274
ለስቲዲዮ መኝታ ቤት ብር 151
በአዲስ  20 በ 80
ለባለ 3 መኝታ ቤት ብር 489
ለባለ 2 መኝታ ቤት ብር 401
ለባለ 1 መኝታ ቤት ብር  196
ለ10 በ 90

የመጀመሪያ የቁጠባ መጠን ብር 187 ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ሳይቋረጥ በተከታታይ  ለ 2 አመታት መቆጠብ ይኖርበታል

Sunday, May 12, 2013

የአቶ ገብረዋህድ ባለቤት በቁጥጥር ስር ዋሉ

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ባለቤት ኮሎኔል ሃይማኖት ተስፋይ ባለቤታቸው ከተጠረጠሩት ወንጀል ጋር ተያያዥ የሆኑ ሰነዶችን ሲያሸሹ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ከፖሊስ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ኮሎኔል ሃይማኖት ከመኖሪያ ቤታቸው ወስደው በሌሎች ግለሰቦች እጅ እንዲደበቁ ያሸሻቸው ሰነዶች በተለያዩ ቦታዎች በአቶ ገብረዋህድ ስም የተመዘገቡ የቤትና የቦታ ካርታዎች ናቸው፡፡
ኮሎኔል ሃይማኖት ካርታዎችን ሲያሸሹ ጥቆማ የደረሳቸው የደህንነትና የፖሊስ ሃይሎችም ክትትል በማድረግ ካርታዎቹን ከተደበቁበት ቦታ ይዘዋቸዋል፡፡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ግንቦት 2/ 2005 በቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች ቤት በተደረገው ብርበራ ከፍተኛ መጠን ያለው የኢትዮጵያና የውጭ ሃገራት ገንዘብ እንዲሁም የተለያዩ ሰነዶች መገኘታቸው ይታወሳል፡፡

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች ቤት የንብረትና የሰነድ ማስረጃዎች ተገኙ

n     ግንቦት 4/9/2005 በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች መኖሪያ ቤት ፖሊስ ባደረገው ብርበራ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተገኘ።
  ከገንዘብ በተጨማሪ በርካታ የቤት ካርታዎች፣የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችና ሌሎችም ከወንጀሉ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የሰነድ ማስረጃዎች ተገኝተዋል።
የፌዴራል ፖሊስ  የፍርድ ቤት ማዘዣ በማውጣት ታዛቢዎችና ተጠርጣሪዎቹ ራሳቸው በተገኙበት ነው በትናንትናው እለት በግለሰቦቹ ቤትና መስሪያ ቤት ብርበራ ያካሄደው።
    ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንዱ በሆኑት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት በተደረገው ብርበራ 8 ላፕቶፖችን ጨምሮ 200 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ፣26 ሺህ 300 የአሜሪካን ዶላር፣19 ሺህ 435 ዩሮ ፣560 ፓውንድና 210 የታይላንድ ገንዘብ  ተገኝቷል፡፡  ከዚህም በተጨማሪ በለገዳዲና ለገጣፎ የሚገኙ የቦታ ካርታና ፕላን እንዲሁም የተለያዩ ሰነዶች መገኘታቸውን ፖሊስ አስታውቋል፤


        የፌዴራል ፖሊስ እንዳለው የቃሊቲ ጉምሩክ ኃላፊ በነበሩት ሌላኛው ተጠርጣሪ አቶ አስመላሽ ወልደማርያም ቤትም እንዲሁ ወደ 2 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ  በጥሬው ተገኝቷል። አቶ አስመላሽ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ውስጥ የጉምሩክ ስነ ስርዓት አፈጻጸም የስራ ሂደት፣የኤርፖርት የኤርጉምሩክ የድህረ ክሊራንስ ኦዲት የስራ ሂደትና የኤርፖርት ጉምሩክ ስነ ስርዓት ቡድን መሪ በመሆን ጭምር ሲያገለግሉ የቆዩ ናቸው። 

      ተጠርጣሪዎቹን ለህግ ለማቅረብ ከፌዴራል የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመሆን የተካሄደው ጥምር ዘመቻ በእቅድ የተመራ፣ህጋዊ ስርዓትን መሰረት ያደረገና የተሳካ እንደነበር የፌዴራል ፖሊስ ገልጿል። በሂደቱም ከወንጀሉ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያላቸው ማስረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ነው በፌዴራል ፖሊስ የፋይናንስ ነክ ወንጀሎች ቡድን መሪ ኢንስፔክተር በለጠ ባለሚ የተናገሩት። በቀጣይም ፖሊስ በምርመራ ሂደቱ የደረሰበትን መረጃ ለህዝብ እንደሚያሳውቅና ህብረተሰቡም ህግን ለማስከበርና ሙስናን ለመዋጋት መንግስት በሚያደርገው ጥረት ተሳትፎውን እንዲያጠናክር የፌዴራል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ኮሚሽኑ በቁጥጥር ስር የዋሉትን የ13 ተጠርጣሪዎችን ስም ይፋ አደረገ

g ግንቦት 3/9/2005  የፌደራሉ የስነ-ምግባር ጸረ ሙስና ኮሚሽን በቁጥጥር ስር የዋሉትን  የ 13 ተጠርጣሪዎች ስም በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል ፡፡  በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ ከፍርድ ቤት ህጋዊ የብርበራና የእስር ትእዛዝ በማውጣት

1. የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር   አቶ መላኩ ፈንታን

2. ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ 

         3. እሸቱ ወልደሰማያት - በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
        4. አስመላሽ ወልደማሪያም- የቃሊቲ ጉምሩክ ኃላፊ
        5. ጥሩነህ በርታ- በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተወረሱ ንብረቶች አስተዳደር ቡድን መሪ
        6. አምኘ ታገለ- የናዝሬት ጉምሩክ ኃላፊ
        7. ሙሉጌታ ጋሻው- በኦሮሚያ ልዩ ዞን መሀንዲስ
        8. ከተማ ከበደ- የኬኬ ትሬዲንግ ባለቤት
        9. ስማቸው ከበደ- የኢንተርኮንቴንታል ሆቴል ባለቤት
      10. ምህረት አብ አብርሀ- ባለሀብት
      11. ነጋ ገብረእግዚአብሄር- የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት
     12. ዘሪሁን ዘውዴ -ትራንዚተርና ደላላ
    13. ማርሸት ተስፉ - ትራንዚተርና ደላላ  በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

Tuesday, May 7, 2013


Debrebrhan Hospital expanding by over 350 million Br

Debrebrhan Hospital expanding by over 350 million Br
       Expansion of the Debrebrhan Referral Hospital, which is located in North Shoa Zone of Amhara State, is happening with over 350 million Birr. This is according to ENA. Recently Minister of Health, Dr. Keseteberhan Admassu gave a visit to the hospital. The hospital has been in service for the last 76 years. The expansion is aimed at providing improved health service to the increasing number of the public in the city and around.

     Documents say the expansion is to come to end in the next six years.  Now the first phase of the expansion is already finalized. Upon completion of the expansion the hospital, which will have over 300 beds, wards for outpatient, delivery, emergency and surgical operations, among others, will benefit more than 2.4 million customers.The regional health bureau and the Ministry of Health finances expansion of the Hospital. Dr. Keseteberhan upon his visit reaffirmed the will of his office to provide the the necessary support to up and run operations of the Hospital.

   Similarly, ENA reports the Organization for Rehabilitation and Development in Amhara (ORDA) sets to build 22 small-scale irrigation projects at a cost of over 73 million Birr this budget year. ORDA’s reportedly is up to boost agricultural development in the state to benefit farmers through irrigation development. The projects will help farmers make use of surface and ground water resources to increase productivity in the state.

World Bank, AFDB to Fund $1.26 Billion Ethiopia-Kenya Power Line

World Bank, AFDB to Fund $1.26 Billion Ethiopia-Kenya Power Line
   
   The World Bank and African Development Bank will provide 80 percent of the funds needed for a $1.26 billion line that will take power to Kenya from Ethiopia, Bloomberg reported. The World Bank will lend the countries $684 million for the 1,070-kilometer (665-mile) line that will run from Wolayta-Sodo in Ethiopia to Suswa, 100 kilometers northwest of the Kenyan capital, Nairobi, African Development Bank Regional Director Gabriel Negatu told reporters today in the city. The AFDB is lending $338 million, he said. “The interconnection with Ethiopia will ensure access to reliable and affordable energy to around 870,000 households by 2018,” Negatu said.

      Four out of every five Kenyan households light their homes with kerosene lamps because they aren’t linked to the national grid, which doesn’t reach many rural communities. Ethiopia, which according to the World Bank has the highest hydropower potential in Africa after the Democratic Republic of Congo, hopes to finish the self-funded $5 billion Nile dam in 2018, which will be the continent’s biggest power plant. Kenya plans to spend as much as $50 billion over the next 20 years to meet a 14 percent annual increase in electricity demand, according to the country’s energy regulator. The nation, which has East Africa’s biggest economy, will need 16,905 megawatts annually by 2031 from 1,520 megawatts this year, the regulator said.
 
    The line will have capacity to carry 2,000 megawatts, with the power sources from hydroelectric projects in Ethiopia, Negatu said. One megawatt is enough electricity for 500 to 1,000 U.S. homes. Agence Francaise de Developpement, the French agency that provides financing to emerging-market countries, will make $118 million available for the project, while Kenya will contribute $88m and Ethiopia $32 million, Negatu said.
Construction of the line will start in September, he said.