Wednesday, December 10, 2014

የመጀመሪያውን የአውሮፕላን በረራ ስልጠና የወሰዱት እነማን ናቸው….?


  በኢትዮጵያ በ1922ዓ.ም በጅግጅጋ ከተማ የመጀመሪያው የአውሮፕላን በረራ ት/ቤት በፈረንሳዊው ሙሴ ጋስቶን ቨርዲየር መምህርነት ተቋቋመ፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያውን የአውሮፕላን በረራ ስልጠና የወሰዱት ኢትዮጵያውያን፡-

1.  አስፋው አሊ
2.  ሚሽካ ባቢችፍ /በአባት ሩሲያዊ በእናት ኢትዮጵያዊ/
3.  ስዩም ከበደ
4.  ባህሩ ካባ
5.  ደምሴ ኃይለኢየሱስ
6.  ደመቀ ተክለወልድ

7.  ወ/ሮ ሙሉመቤት እምሩ ናቸው፡፡

   አስፋው አሊ እና ሚሽካ ባቢችፍ በመጀመሪያ ስልጠናቸውን በማጠናቀቅ ጥቅምት 3 ቀን 1923ዓ.ም ከንጉሰ ነገስቱ እጅ የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡ ት/ቤቱም ስራውን የጀመረው በሁለት አውሮፕላኖች ነበር፡፡


   በኢትዮጵያ አቭዬሽን ታሪክ የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያውያን አውሮፕላን አብራሪዎች አስፋው አሊ እና ሚሽካ ባቢችፍ ናቸው፡፡ ሁለቱም የብቻ በረራቸውን ያካሄዱት በ1923ዓ.ም ነበር፡፡
  
  እ.ኤ.አ በ1935 የታተመው የአሜሪካ ጋዜጣ ስናፒ ላንዲንግ ሌዲ በርድ የሚል አድናቆት የሰጣቸው ወ/ሮ ሙሉመቤት እምሩ የመጀመሪያዋ የሴት አውሮፕላን አብራሪ ናቸው፡፡ የመጀመሪያውን የብቻ በረራ ያካሄዱት በ1927ዓ.ም ነበር፡፡ ወ/ሮ ሙሉመቤት እምሩን አውሮፕላን መንዳት በማስተማር ታሪክ የመጀመሪያይቱ አፍሪካዊትም እንዲሆኑ ያስቻሏቸው ኮለኔል ጄ.ሲ.ሮ.ቢንሰን የተባሉ ጥቁር አሜሪካዊ ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment