Sunday, December 7, 2014

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት አዲስ የአለም ክብረ ወሰን አስመዘገበ፡፡






  ኢትዮጵያ  በታላቁ  ህዳሴ  ግድብ  ግንባታ  ፕሮጀክት  24 ሰዓት  ውስጥ  16 ሺህ 949  ሜትር  ኪዩብ  አርማታ  በመሙላት   የአለም  ክብረ  ወሰንን  ሰበረች። 9ኛው  የብሄር ብሄረሰቦች  በዓል  ዋዜማ  ትናንት  ምሽት  የህዳሴው  ግድብ  በሚገነባበት  ጉባ    ወረዳ  ባምዛ  ቀበሌ  ተከብሯል፡፡ 


  የዋዜማ በዓሉ ላይ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ እንደገለፁት፥ ከዚህ ቀደም 24 ሰዓት ከፍተኛ የአርማታ  ሙሌት  በማካሄድ  የአለም   ሪኮርድ  የተመዘገበው  በቻይና  ሀገር  የሃይል  ማመንጫ  ግንባታ  ሲሆን፥ መጠኑ  16 ሺህ 800  ሜትር  ኪዩብ  ነበር።ህዳር  20  ቀን  2007 .  በህዳሴው  ግድብ  ፕሮጀክት  በተካሄደ  የአርማታ  ሙሌት  24 ሰዓት  ውስጥ  16 ሺህ 949  ሜትር  ኪዩብ  አርማታ  በመሙላት  ኢትዮጵያ  ሪከርዱን  መስበር  መቻሏን  ኢንጂነር  ስመኘው  ተናግረዋል።

   በጠቅላለው 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትር ኪዩቢከ አርማታ የሚሞላበት የህዳሴው ግድብ ግንባታ ስራው ሲጠናቀቅ 145 ሜትር ከፍታ እና 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይኖረዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ 60 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ በላይ ውሃ በመያዝ 6 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም ሲኖረው በትልቅነቱ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ደግሞ ሰባተኛ ደረጃን ይይዛል።

No comments:

Post a Comment