Tuesday, December 2, 2014

የአፍሪካ ህብረት ለዶክተር ሳሊም አህመድ ሳሊም የክብር ማዕረግ ሰጠ

  የአፍሪካ ህብረት የፀጥታና ደህንነት ኢንስቲትዩት ለቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ዶክተር ሳሊም አህመድ ሳሊም የክብር ማዕረግ ሰጠ፡፡ ዶክተር ሳሊም አህመድ ሳሊም የክብር ማዕረጉን ያገኙት በሀገራቸውም ሆነ በአፍሪካ ደረጃ ለነጻነት፣ ለሰላምና ለፍትህ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ነው፡፡
   በአፍሪካ ህብረት በተካሄደ ስነ ስርዓት የተሰጠው የክብር ማዕረግ ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሞክሮ ይሆናል ተብሏል፡፡ የ72 ዓመቱ ታንዛኒያዊው ዲፕሎማት ያገኙት የክብር ማዕረግ ለአህጉሪቱ ሁለንተናዊ ለውጥ የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ ለማጠናከር እንደሚረዳቸው ገልጸዋል፡፡ ዲፕሎማቱ ከዚህ በፊት ለሰሩት በጎ ተግባር 20 የተለያዩ የክብር ማዕረግና ዲግሪ ተበርክቶላቸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment