Saturday, December 6, 2014

ብሩክታይት ጥጋቡ የ2014 የትሬምፕሊን ሽልማት አገኘች

  
   የዊዝ ኪድስ ኢትዮጵያና "ጸሐይ መማር ትወዳለች" የህጻናት የቴሌቪዥን ፕሮግራም መስራች ብሩክታይት ጥጋቡ 2014 የትሬምፕሊን ሽልማት አሸናፊ ሆነች፡፡ የዊዝ ኪድስ ወርክሾፕ መስራችና ስራ አስኪያጅ የሆነችው ብሩክታይት ጥጋቡ በማህበራዊ ዘርፍ የተሰማሩ የቢዝነስ ፕሮጀክቶችን የሚያበረታታው 2014ቱን የትሬምፕሊን ሽልማት መሸለሟ ታውቋል፡፡ ከዩኔስኮ ጋር በትብብር የሚሰጠው ይህ ሽልማት 10 000 ዶላር የገንዘብ ሽልማት፣ የአንድ አመት የዓለማቀፍ የማማከር ድጋፍ እንዲሁም የሚዲያ ሽፋን ማግኘትን የሚያካትት ነው ተብሏል፡፡



  የብሩክታይት ስራ የሆነው "ፀሐይ መማር ትወዳለች" አስተማሪ የሕጻናት የቴሊቪዥን ፕሮግራም ከቴሌቪዥንም በተጨማሪ ከትምህርት ቤቶች እስከ ስደተኞች ጣቢያ ድረስ በአማካይ 5 ሚሊየን ሕጻናት አይተውታል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህ "ፀሐይ መማር ትወዳለች" የተባለው ትምህርታዊ ፕሮግራም የጃፓኑን International Contest for Education Media .. 2008 ደግሞ Next Generation Prize at Prix Jeunesse International እንዲሁም 2011 የማይክሮሶፍትን Microsoft Education Award አሸንፏል፡፡  ብሩክታይት 2010 የሮሌክስ ወጣት ሌሬትም ተብላ መሰየሟም ይታወሳል፡፡

No comments:

Post a Comment