Sunday, February 2, 2014

የአፍሪካ ህብረት የጤና ማዕከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

 ህብረቱ በ22ኛ መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ባሳለፈው ውሳኔ የአፍሪካ የጤና ማዕከልን ለመገንባት መሪዎቹ  በናይጀሪያ አቡጃ በተስማሙት  መሰረት የአህጉሪቱን ታላቁ የጤና ማዕከል በአዲስ አበባ ይገነባል ፡፡

 የጤና  ማዕከሉ የምርምር፣የምክርና አፍሪካን የሚመለከቱ ማንኘውንም  ጤና ነክ  ጉዳይ  በበላይነት የሚቆጣጠር ይሆናል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ጥር 23 ማመሻውን የተጠናቀቀ ሲሆን በመሪዎቹ የሁለት ቀንናት ቆይታም ከ2014 እስክ 2017 የሚዘልቅ የአፍሪካን የልማት  ስትራቴጅክ እቅድ ተወያይተው አፅድቀዋል፡፡

  መሪዎቹ በአፍሪካ  ሰላምና መረጋጋት፣ በግጭት ቀጠናዎች፣ አፍሪካ ከሌሎች አጋር አካላት  ጋር ያላትን ትስስር እንዲሁም  በግብርናና በምግብ ዋስትና መክሯል፡፡ የቀጠዩ የአፍሪካ  ረት 23ኛው የመሪዎች ጉባኤ  ሃምሌ ወር ላይ በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ይካሄዳል፡፡

No comments:

Post a Comment