Friday, February 7, 2014

ገንዘቤ ዲባባ የ3000 ሜትር የቤት ውስጥ ሪከርድን ሰበረች


    የ5ሺህ ና 10ሺ ሜትር ንግስት  የጥሩነሽ ታናሽ የሆነችው ገንዘቤ ድባባ በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ግዜ የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ክብረ ወሰን  በሲዊድን  ስቶክሆልም ለመጨበጥ በቅታለች፡፡

  የ22 አመቷ አትሌት ገንዘቤ ድባባ በ3ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ነው በ5 ቀን ልዩነት ሁለተኛ ድሏን ያጣጣመችው፡፡ አትሌት ገንዘቤ በዚሁ ርቀት በ7 ሰከንድ ያሻሻለችው ክብረወሰን በሀገሯ ልጅ መሰረት ደፋር ለ7 አመት ያህል 8፡23፡72 ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ነው፡፡ገንዘቤ ርቀቱን 8፡16፡60 በሆነ ሰአት አለምን በማስደመም ለሁለተኛ ጊዜ በቤት ውስጥ የሩጫ ሻምፒዮና ለመንገስ በቅታለች፡፡

  ገንዘቤ ከአምስት ቀን በፊት በተመሳሳይ በ1500 ሜትር የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ክብረ ወሰን ማስመዝገቧ ይታወሳል፡፡ በዚህ ውድድር ከ1993 ጀምሮ ቻይናዊያኑ ትሪዮ ዋንግ ጁንሺያ ፣ ቁ ዩንሺያ እና ዣንግ ሊንሊ ጥሩ ተፎካካሪዎች ነበሩ።
                                                    ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

No comments:

Post a Comment