Sunday, February 16, 2014

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በእንግሊዝ በርሚንግሃም በተካሄደው ውድድር አዲስ ሪከርድ አስመዘገበች

 
        የ23 ዓመቷ ገንዘቤ ዲባባ በእንግሊዝ በርሚንግሃም የተካሄደውን የ2 ማይልስ የሩጫ ውድድር በ 9 ደቂቃ ከ48 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት በ15 ቀን ልዩነት ሶስተኛውን ሪከርድ ሰብራለች።
   
   ቀደም ሲል በሳምንት ውስጥ በስቶኮልም ከተማ በተካሄደው የቤት ውስጥ ውድድር 1500 ሜትሩን 3: 55: 17 በመግባት በ3 ሰከንድ ልዩነት የቀድሞውን ክብረወሰኑን የሰበረች ሲሆን ፥ በጀርመን በተካሄደው የ3000 ሜትር የአለም የቤት ውስጥ ውድድርም ርቀቱን 8: 16: 23 በመግባት በ7 ሰከንድ ዳግመኛ የአለም ክብረ ወሰን በመስበር የዓለምን ትኩረት ስባለች።

No comments:

Post a Comment