Saturday, September 24, 2022

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የክብር ዶክትሬታቸውን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተቀበሉ።


 ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው በዩኒቨርሲቲው የተበረከተላቸውን የክብር ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል። ብፁዕነታቸው ለሐዋርያዊ አገልግሎት ከሀገር ውጭ ስለ ነበሩ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነሐሴ 21 ቀን 2014 . የሰጣቸውን የክብር ዶክትሬት በአካል ተገኝተው መቀበል አልቻሉም ነበር፡፡

የክብር ዶክተር ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፥ አሸባሪው ሕወሓት ሰሜን ወሎን በወረራ ይዞ በነበረበት ወቅት ለተራቡት አብልተዋል፣ ለተጠሙት አጠጥተዋል፣ ለታረዙት አልብሰዋል፤ ያዘኑትን አጽናንተዋል። 5 ወራት በቆየው ወረራ የወልድያና አካባቢውን ሕዝብ ሃይማኖት፣ ዘር፣ ቋንቋ ሳይመርጡ ክፉ ቀንን አሳልፈዋል። በዚህም ወላዶች፣ ቁስለኞች፣ በችግር ላይ የነበሩ ወገኖች ከጉዳት ተርፈው መልካም ቀንን እንዲያዩ አድርገዋል። ይህ ስራቸውም የክብር ዶክትሬት እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ (የክብር ዶክተር) በበኩላቸው "ሁሉ ከእርሱ፣ ሁሉ በእርሱ፣ ሁሉም ለእርሱ በመሆኑ የመከራው ቀን አልፏል፤ የተሰጠኝ የክብር ዶክትሬት ወገኑን ለማትረፍ መልካም ነገርን ሁሉ ላደረገ ሕዝብ ነው" ብለዋል። ብፁዕነታቸው በወቅቱ 5 ወራት እህል፣ ውኃ፣ ልብስ፣ መብራት በሌለበት ወቅት ችግር ላይ ወድቆ የነበረን ሕዝብ በእግዚአብሔር ድጋፍ ወደ ሰላም እንዲመለስ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት / ፍሬው ተገኘ በበኩላቸው "ብዙዎች ከአካባቢያቸው በሚሸሹበት ወቅት በጦርነት ውስጥ ወደ ሚገኘው ሕዝባቸው በመሄድ የመከራ ቀን እንዲያልፍ ታሪክ የማይረሳው ሥራን ሠርተዋል" ብለዋል። በዚህም የከበረ ሥራን አከናውነው የከበሩትን በማክበራችን እኛም ብዙ አትርፈናል በማለት ገልጸዋል፡፡

ልጇ ክብር በማግኘቱ ቤተክርስቲያን ደስ ብሏታል ያሉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው። ከዲቁና እስከ ሊቀ ጵጵስና ድረስ በትክክል የበጎች እረኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ሲሉም ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

ከሀገር ውጭ የነበሩት ብፁዕ ኡቡነ ኤርምያስ ዛሬ ረፋዱን ወደ ባሕርዳር ሲገቡ ብፁዓን አባቶች፣ ሊቃውንት፣ የመንግስት ባለስልጣናት እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በባሕር ዳር ዓለም አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ባለፈው ነሐሴ 21/2014 . ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለብፁዕ አቡነ ኤርምያስና ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የክብር ዶክትሬት መስጠቱ ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment