Wednesday, September 14, 2022

ስለ አቤቱ ነጋሴ ክርስቶስ ወረደ ቃል 2ኛደረጃ ት/ቤት ምን ያህል ያውቃሉ?


የሰው ልጅ ከነበረበት ኋላ ቀር የአደንና የዋሻ ኑሮ ተላቆ ወደ ተሻለ የአኗኗር ዘዴ ለመግባት በጥልቅ ኑሮው ላይ መሰረታዊ የሆኑ ለውጦችን በማድረግ አሁን ካለበት የስልጣኔ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ለዚህም ሽግግር ትምህርት፡እውቀት፡ ምርምር እና ጥረት አይነተኛው መሳሪያ በመሆን ትልቁን አስተዋፅኦ ማሳረፍ ችለዋል፡፡ በየጊዜውና በየወቅቱ የተከፈቱ ትምህርት ቤቶችም የትምህርት እና የእውቀት ማዕከል በመሆን የሰውን ልጅ ሽግግር ለማፋጠን የእውቀት ብርሃን ሲረጩ ቆይተዋል፡፡

በታሪክ በመንዝና ግሼ አዉራጃ የመጀመሪያ የሆነዉ /ቤት የመሰረት ድንጋዩ የተጣለዉ ሚያዝያ 7/1940 . በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ነበር፡፡ ንጉሱም በወቅቱ የመንዝ አርበኞች በአምስት አመቱ የፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግል ከኢጣሊያን ወራሪ ጦር ጋር በአርበኝነት ላደረጉት ተጋድሎ ለመታሰቢያ እና ለምስጋና ይሆን ዘንድ ለአዉራጃዉ ህዝብ /ቤቱን አስከፍተዋል፡፡ የግንባታዉ ስራ በኢጣሊያ መሃንዲሶችና ግንበኞች አማካኝነት ሲገነባ የመጀመሪያዎች ግንባታዎችም ሶስት ብሎኮች ነበሩ፡፡ እነሱም የፊት ለፊቱ የፎቁ ህንፃ ከጀርባዉ ያለዉ ባለ U ሼፕ ረጅሙ ህንፃ እና የዉሃ ታንከሩ አጠገብ ያለዉ አሁን ለዲፓርትመንቶች እና ለክበባት ቢሮዎች አገልግሎት የሚሰጠዉ ህንፃዎች ናቸዉ፡፡ ለግንባታ የሚሆኑ የግንባታ ቁሳቁሶች ከጣርማ በር በአካባቢዉ ነዋሪዎች በሸክምና በአህያ ሲመጡ አሸዋ ደግሞ ከሞፈር ዉሃ በማምጣት እስከሁን ድርስ የቆዩ እና ባለግርማ ሞገስ ህንፃዎችን ለመገንባት ተችሏል፡፡ ሁለት አመት የፈጀው የግንባታ ሂደት በጊዜው ተጠናቆ የመጀመሪያዎቹን 30 ተማሪዎች በመቀበል 1942. ስራውን ጀመረ፡፡ እነዚህ 30 ተማሪዎች በወቅቱ አለቃ አርምዴ በሚባሉ የቤተ - ክህነት መምህር ጣሊያን በሰራት ቤት ዉስጥ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ነበሩ፡፡ (ያቺ ጣሊያን የሰራት ቤት ቀድሞ አብዮት አደባባይ የነበረዉ ቦታ ከቀድሞዉ ፖሊስ ጣቢያ አጠገብ የነበረች እንዲሁም ታደሰ ገናዬ ነዳጅ ይሸጡባት የነበረች እንደ ስቴዲየም ትሪቡን የመሰለ ጣራ የነበራት ባለ አንድ ፎቅ ህንፃ ነበረች፡፡ አሁን የመምህራን ማህበር ህንፃ ተሰርቶበታል)፡፡ ሆኖም የተማሪዎቹ ወላጆች በእኚህ መምህር ላይ እምነት ስላልነበራቸዉ /ቤቱ ተሰርቶ እንደተጠናቀቀ ዝዉዉር ጠይቀዉ ከአካባቢዉ ለቀዉ ሄደዋል፡፡


ከዚያም በኃ/ማርያም ማሞ /ቤት የተማሪዎች ሞግዚት፤ በመቀጠል የካራ ቆሬ መምህር ሆነዉ ያገለግሉ የነበሩት የኔታ ዳምጠዉ የትምህርት ቤቱ የመጀመሪያ ዳይሬክትር በመሆን ቀደም ሲል የነበሩትን 30 ተማሪዎች በመረከብ የትምህርት ቤቱን ስራ በይፋ አስጀምረዋል፡፡ የኔታ ዳምጠው መኮንን አዳዲስ መምህራን ተመድበው ሲመጡ ከህብረተሰቡ ጋር በማስተዋወቅ፤ አካባቢውን በማለማመድ፤የስራ ልምዳቸውን በማካፈል ዘመናዊ ትምህርት በመንዝ ምድር እንዲስፋፋ ገበሬውም ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልክና በአጠቃላይ የትምህርት ጥቅም እንዲታወቅ ያደርጉ የነበሩ ትልቅ ሰው ነበሩ፡፡ በወቅቱም በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ልጆችን ወደ ዘመናዊ ትምህርት ቤት ማስገባት በበጎ አይን ስለማይታይ ይባስ ብሎም ሃይማኖታቸውን ወደ ካቶሊክ ይቀይራሉ ተብሎ ስለሚታሰብ ተማሪዎችን እንደልብ ማግኘት አዳጋች ነበር፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍም የቤተ - ክህነት መምህሮችን በትምህርት ቤቱ ውስጥ የአማርኛ እና የግብረ-ገብ (the modern day Civics and Ethical Education) አስተማሪ አድርጎ በመመደብ በነባሩና በዘመናዊው የትምህርት መድረክ ላይ እንደ ድልድይ በመጠቀም በማህበረሰቡና በቤተክህነት አካባቢ ያለውን ችግር ረገብ ለማድረግ ተችሏል፡፡

የትምህርት ቤቱ አስተዳደር እና የበላይ አካልም ይህንን ችግር ለመቅረፍ በማሰብ 30 ተማሪዎች ቁምጣና ኮት በማሰፋት ተማሪዎች ይህንን ልብስ እየለበሱ በሞላሌና በአካባቢው በሚገኙ ቤተክርስቲያኖች የንግስ በአል ላይ በመገኘት የተለያዩ ቀስቃሽ መዝሙሮችን በመዘመር ብዙ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ለማድረግ ተችሏል፡፡ ታዋቂ ከነበሩት መዝሙሮች ውስጥም -

ተማር ተማር አትማርም ወይ

በግ እረኛነት ይሻልሃል ወይ

እሺ እሺ እማራለሁ

በግ እረኝ ነት መች እወዳለሁ፡፡ የሚለው ይጠቀሳል፡፡ በኋላ ላይ ትምህርት ቤቱ የአዳሪ ትምህርት በመጀመር 60 ተማሪዎች በጀት ተፈቅዶ ስራውን ቀጥሏል፡፡ ፍራሽ፡ አንሶላ እና አልጋ ከደብረ ብርሃን ተገዝተው ሲመጡ ለብርድ ልብስ የሚሆን ባና (the local blanket) ደግሞ ከአካባቢው እንዲገዛ ተደረገ፡፡

በወቅቱ የነበሩት ተማሪዎች እንደሚያስታውሱት የአዳሪ ትምህርት ቤቱ በደንብና በስርዐት የሚመራ ከአሁኑ ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ስርዐት ጋር ተቀራራቢ የሚባል አስተዳደር እንደነበረው ይናገራሉ፡፡ የምግብ ሰዐት የተወሰነ ሲሆን ቁርስ፤ ምሳ እና ራት በተቀመጠው ሰዐት ይከናወናል፡፡ ጠዋት ቁርስ ከተበላ በኋላ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር የሰንደቅ አላማ ማውጣት ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡ የምግብ ሜኑዎቹም ማካሮኒ፡ ምስር፡ የስጋ ወጥ፡ ክክ እና ጎመን ነበሩ፡፡ ይህም ከገጠር ለመጣ ልጅ ያለምንም ስራ በመማርና በማጥናት ብቻ መመገብ መቻል እንደ ተአምር ይቆጠር እንደነበር ጨምረው ያስታውሳሉ፡፡ በተጨማሪም ለአንድ ተማሪ በወር 5 ብር ደሞዝ ይቆረጥለት የነበር ሲሆን የአዳሪ ትምህርቱ እስከቆመበት እስከ 1953 . ድረስ የአንድ ተማሪ ደሞዝ 25 ብር ደርሶ ነበር፡፡


በጊዜ ሂደትም የተማሪዎች ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ ከሀገር ውስጥ መምህራን በተጨማሪ የውጪ መምህራንም ተመድበው ሰርተዋል፡፡ ከውጭ መምህራኖቹ በአብዛኛው የሚጠቀሱት ህንዳዊያን ናቸው፡፡ ከየኔታ ዳምጠው ቀጥሎ የነበሩ የሀገር ውስጥ መምህራን - ቄስ አፈወርቅ ተሳንቴ፣ መምህር ባንጃው መምህር ፀጋዬ ወልደአማኑኤል እና አለቃ ይትባረክ ካሳ ሲሆኑ ተቋሙን 5/አምስት/ የህንድ ርዕሠ መምህራን መርተውታል፡፡ እነሱም፡-ሚስተር ቦዘቦኒካም፣ ሚስተር ፖል፣ ሚስተር ፒር መሃመድ፣ ሚስተር ጋናፒቲ እና ሚስተር ሳይመን በጊዜው በነበሩት ተማሪዎች ዘንድ የሚታወሱ ናቸው፡፡ይህ ትምህርት ቤት ስራውን ከጀመረበት 1942 እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ለማህበረሰቡ ትምህርት በመስጠት ለመንዝና ለአካባቢው ህዝብ ሰፊ አሻራ ማስቀመጥ የቻለ እጅግ ትልቅና ታሪካዊ ተቋም ነው፡፡ አሁን የያዘውን ቅርፅ ከመያዙ በፊት በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች ሲያስተምር ቆይቷል፡፡

- 1942 - 1947 . 1 - 6 ክፍል

- 1948 - 1966 . 1 - 8 ክፍል፤ በወቅቱም ስምንተኛ ክፍልን የጨረሱ ተማሪዎች በአብዛኛው ወደ ሐረር እና ሌሎች በዘመኑ ወደነበሩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይላኩ ነበር፡፡

በጊዜው በኢትዮጵያ የነበሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብዛታቸው ስምንት ነበር፡፡ እነርሱም ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (የአሁኑ ኮተቤ ዩኒቨርሲቲ) ጀኔራል ዊንጌት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተፈሪ መኮንን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መድሃኔአለም(ባላባት) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ዳግማዊ ምኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሐረር መድሃኔአለም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮከበ ፅባህ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና እቴጌ መነን (ሴቶች ብቻ ይማሩበት የነበረ) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ናቸው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ሰባቱ አዲስ አበባ ሲሆኑ አንዱ ደግሞ ሀረር ነበር፡፡

- 1967 - 1987 1 - 12 ክፍል ሲሰጥ ቆይቶ ቀደም ብሎ 1978 . አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎድጓዲት በመከፈቱ 7-12 ክፍል ድረስ ሲያስተምር ቆይቷል፡፡

- 1988 - 1990 በመቀጠልም የአሁኑ የመሰናዶ /ቤት በመከፈቱ 9 - 12 ትምህርት ቤት ተዛውሯል፡፡

- 1991 - 1996 . 1 - 8 ክፍል ፤ከ1996 . እስከ አሁን ድረስ ደግሞ 9 - 10 ክፍል ትምህርት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ይህ ትምህርት ቤት ከምስረታው ጀምሮ የተለያዩ ስያሜዎች ተስጥተውት ነበር፡፡

Ø 1940 - 1954 . - ቀዳማ ኃይለስላሴ /ቤት

Ø 1955 - 1970 . አቤቶ ነጋሲ ክርስቶስ ወረደ ቃል /ቤት

Ø 1970 - 1989 . ሞላሌ ከፍተኛ 2 ደረጃ /ቤት

Ø 1990 - 1994 . ሞላሌ አንደኛ እና መለስተኛ ደረጃ /ቤት የሚሉ ናቸው፡፡

ከስያሜዎቹ ሁሉ በብዙ የቀድሞዎቹ ተማሪዎች ዘንድ በጉልህ የሚታውቀው አቤቶ ነጋሲ ክርስቶስ ወረደ ቃል የሚለው ስያሜ ነው፡፡ 1967 የደርግ መንግስት ወደ ስልጣን መምጣቱን ተከትሎ ጥንታዊና ታሪካዊ የሆኑትን ስያሜዎች የፊውዳል ስርዐት ቅሪቶች ናቸው በማለት ስያሜያቸውን ሲቀይር የትምህርት ቤቱ ስያሜ ሊቀየር ተችሏል፡፡ በተለያየ ጊዜ በዚህ ስም እንዲጠራ ጥያቄ ሲቀርብ ቆይቶ የመንዝ ማማ ወረዳ ምክር ቤት ጥቅምት 6/2012 ባደረገው 7 አመት 1 ዙር ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ከአርባ አንድ አመታት በኋላ ወደ ቀደመው ስሙ እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ ይህ እንዲሆን በተለያየ ጊዜ ድምፃቸውን ላሰሙ የቀድሞ ተማሪዎች፡ ለታገሉ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዲሁም ውሳኔውን ላፀደቁት የመንዝ ማማ ወረዳ ምክር ቤት አባላት ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፡፡ 1940. 30 ተማሪዎች እና በአንድ የቅኔ መምህር ስራ የጀመረው ተቋም 2014. 3014 ተማሪዎችን 2 ርዕሰ መምህራን 145 መምህራን እና 15 ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን ይዞ ስራውን ቀጥሏል፡፡ ይህ 74 አመት አንጋፋ እና ታሪካዊ /ቤት አጎንብሶ የጠጋኝ/የወገን ያለህ ይላል፡፡

ዋቢ መፅሃፍት

ü አቤቱ ነጋሲ ክርስቶስ ወረደ ቃል ትምህርት ቤት 50 አመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በአል (1940 - 1994) 1994 . ቦሌ ማተሚያ ድርጅት

ü ሽብሩ ተድላ (2005) ከጉሬዛም ማሪያም እስከ አዲስ አበባ፡ የህይወት ጉዞና ትዝታዬ፡ኢስሊፕስ ማተሚያ ቤት - አዲስ አበባ

ü Donald N. Levine (1965). WAX AND GOLD: Tradition and Innovation in Ethiopia Culture: the University of Chicago press. Chicago

No comments:

Post a Comment