Monday, September 28, 2020

ኩናማዎች እና ባህላዊ እሴታቸው…..

 

የኩናማ ብሄረሰብ በ4 ትውልድ ሀረግ የተከፈለ ሲሆን እነሱም ጉማ፣ ካርዋ፣ ሸዋ እና ሴማ በመባል ይታወቃሉ፡፡ 4ቱም የዘር ሀረጎች ብሄራቸው እና ቋንቋቸው አንድ ቢሆንም እያንዳንዳቸው የሚለዩበት እና የራሳቸው የሆኑ ባህል አላቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የቤት አሰራር ጥበባቸው ነው፡፡

 ለአብነት ቤት አናት ላይ “ቡ” የመሰለ የፊደል ቅርፅ ያለው በትር ከተሰቀለ ዝርያው ከጉማ ነገድ መሆኑ በብሄረሰቡ ዘንድ በግልፅ ይታወቃል፡፡ ሌላው ሁለት የተጣበቁ “ቦ እና ባ” የመሳሰሉ በትሮችን በቤቱ አናት ላይ ከሰየመ ዝርያው የሴማ ነገድ መሆኑን ይረዳሉ፡፡ የካርዋ ነገድ ዝርያዎች ደግሞ ወደላይ የወጣ ዘንግ ቤታቸው አናት ላይ ሲሰቅሉ ፤ የሸዋ ነገድ አባላት በቤታቸው አናት ላይ አጭር ዘንግን በመሰየም የዘር ሀረጋቸውን ያመለክታሉ፡፡


 በዚህ መልኩ ከሩቅ የኩናማ መኖሪያ አካባቢ የመጣ የብሄረሰቡ አባል በእያንዳንዱ ቤት ላይ ያለውን ምልክት እያየ እንደ ነገዱ ዝርያ በቀጥታ ቤት ገብቶ ይስተናገዳል፡፡ በቦታ ርቀት ተለያይተው የሚኖሩ ተመሳሳይ ዝርያ ያላቸው ኩናማዎች ባይተዋወቁም አንድ ነገድ በመሆናቸው ብቻ እንደሚተዋወቁ ሆነው በፍቅር ያላቸውን ተካፍለው በእንግድነት ይስተናገዳሉ፡፡ 

 

 

No comments:

Post a Comment