Thursday, August 20, 2020

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የዓመቱ የፋይናንስ ሚኒስትር ሽልማትን አሸነፉ

 የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በፋይናንሺያል አፍሪክ መጽሄት የዓመቱ የፋይናንስ ሚኒስትር ሽልማት ተበረከተላቸው።


ፋይናንሺያል አፍሪክ በፓሪስ የሚታተም መጽሔት ሲሆን፥ ትናንት በአቢጃን ከተማ በተካሄደ ስነ ስርዓት የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴን የዓመቱ የፋይናንስ ሚኒስትር በማለት ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

በኮትዲቯር የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙሉጌታ ዘውዴ ሚኒስትሩን ወክለው ሽልማቱን ተቀብለዋል።

መጽሔቱ በየዓመቱ 100 ዕውቅ የገንዘብ፣ የፋይናንስና ኢኮኖምርጫ እንደሚያካሂድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በኢኮኖሚክስ መስክም ካርሎስ ሎፔስን የዓመቱ ኢኮኖሚስት ብሎ ስይሟቸዋል።

No comments:

Post a Comment