Wednesday, September 23, 2020

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም እና ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ) የ2020 የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

የዘንድሮው የ“ብሪጅ ሜከር አዋርድ” አሸናፊ የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከታይም መጽሔት የ2020 የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ 100 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካትተዋል።


የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ ከዓለማችን 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል አንዱ ሆነው ሊመረጡ የቻሉት በተለይ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ሁሉም ሰው እኩል የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እንዲያገኝ በያዙት ጠንካራ አቋም ነው ተብሏል። በተጨማሪም፣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ለመከላከል በተደረገው ጥረት የራሳቸውን አበርክቶ ማድረጋቸውም ተጠቃሽ ነው።


ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የ2020 “ብሪጅ ሜከር አዋርድ” ሽልማታቸውን በትላንትናው እለት የተቀበሉ ሲሆን ሽልማቱ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ግንባር ቀደም ሆነው እያገለገሉ ላሉ የጤና ባለሙያዎች መታሰቢያ ይሁንልኝ ሲሉ የምስጋና መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ሌላኛው ተፅዕኖ አሳዳሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የካንዳ ዜግነት ያለው አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ) በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጠ ድምፃዊ፣ ገጣሚ እና የሙዚቃ ፕሮዲውሰር ነው። አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊክንድ) በ2020 በለቀቀው after hours በተሰኘ የሙዚቃ አልበም ተወዳጅነት ማግኘቱ የተነገረ ሲሆን በተለይ Blinding Lights ሙዚቃው በ2020 በፖፕ ሙዚቃ ዘርፍ ተመራጪ መሆኑን መረጃዎቹ ያመለክታሉ።

                                   ምንጭ ፡- ኢ.ቢ.ሲ እና ኤፍ.ቢ.ሲ

No comments:

Post a Comment