Friday, March 20, 2020

አዲስ መጽሐፍ በቅርብ ቀን!!


በምድራችን  ላይ  ከምናውቀው  ሀቅ  የራቁና  ያፈነገጡ፣  ከፊዝክስና ሥነ- ሕይወታዊ  የተፈጥሮ  ህጎችም  የወጡ  እውነቶች  በገሀዱ  ዓለም  መኖራቸውን  ያውቀሉ ?   “ እንዴት? ”  አሰኝተው  አዕምሮን  በጥያቄ  የሚፈትሩ!

የሳይንሱን  ዓለም  በጥያቄ  የወጠሩና  በተደምሞ  ዝም  ያሰኙ  ክስተታዊ  እውነቶችንስ  ምን  ማለት  ይቻላል?

ለመሆኑ  የሰው  ልጅ  አውቄዋለሁ  ብሎ  የተረከውን  ጥንታዊ  ታሪኩንና  ጂኦግራፊን  እንደገና  ለመጻፍ  የሚያስገድደው  ማስተካከያ  ይመጣ  ይሆን?

እንዲህ  ማፈትለኩ  ላይቀር  ማስረጃና መረጃን በማጥፋት አስገራሚ ግኝቶችን ለመደበቅ፣ ለማጥፈትና  እንደሌሉ ለማድረግ  ኃያላኑ የሚሰሩት  ለምን  ይሆን?

በየእለቱ  የማይለይዎትንና  ያለምንም  ማመንታት  “በደንብ  አውቀዋለሁ!”  የሚሉትን  ነገር  “ የለም  አያውቁትም! ”  ቢባሉ  ምን  ይሰማዎታል?  እንደማያውቁት  ቢረዱስ  ምን  ይላሉ? 

Ø   “ፍ ን ግ ጥ”  አንብበው  ይደመማሉ!  በቅርብ  ቀን  ይጠብቁን!   
____________________________
በብዙ  እንቆቅልሽ  ድንቆች  የተሞላች
ቅርብ  መሳይ  ጠሊቅ  በእጅጉ  የራቀች
ምድራችን  ጥያቄ  ረቂቅ  ምስጢር  ነች
የፈጣሪ  ቅኔ  ገና  ያልተፈታች!

Thursday, March 19, 2020

ደራሲ እና መምህር ሲሳይ ንጉሱ…..

1951 . እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ደጃች ውቤ /ውቤ በረሃ/ ነው የተወለደው፡፡ አንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በባልቻ አባነፍሶ ሁለተኛ ደረጃን ደግሞ በአዲስ ከተማ አጠቃላይ /ቤት ተከታትሏል፡፡ከዚያም 1974 . አስመራ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በስነ ፅሁፍ እና ቋንቋ 1977 . የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡ 11 ክፍል እያለጉዞውየተሰኘ ኖቬላን የመጀመሪያ ስራው አድርጎ አሳትሟል፡፡ይህንን ጨምሮ 6 ያህል መፅሃፍትን እስካሁን ለአንባቢያን አድርሷል፡፡


ሰመመንየተሰኘው የረጅም ልብ ወለድ ድርሰቱ ከፍተኛ ተነባቢነትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያገኘለት ስራው ሲሆን በወቅቱም 60 ያህል ቅጂዎች ተሸጠውለታል፡፡በ1978 . የታተመው እና 378 ገፆች ያሉትሰመመንበዩኒቨርስቲ ህይወት ዙሪያ እና በፍቅር ታሪክ ላይ ያተኩራል፡፡ መፅሃፉ የተፃፈው ደራሲ ሲሳይ ንጉሱ በአስመራ ዩኒቨርሰቲ 3 አመት ተማሪ እያለ ነበር ፡፡
የደራሲው ሥራዎች፡-
1. ጉዞው ( ኖቬላ ) – 1975 .
2.
ሰመመን ( ልብ ወለድ ) – 1977/8 .
3.
ግርዶሽ ( ልብ ወለድ ) – 1981 .
4.
ትንሳኤ ( ›› ›› ) – 1983 .
5.
የቅናት ዛር ( ›› ›› ) – 1988 .
6.
ረቂቅ አሻራ ( ›› ›› ) – 1995 .
 “ሰመመንየተሰኘው ድርሰቱን በኩራዝ አሳታሚ ድርጅት ሲያሳትም፤ ግርዶሽ፣ ትንሳኤ፣ የቅናት ዛር እና ረቂቅ አሻራን በአርቲስቲክ እና ሜጋ ማተሚያ ድርጅቶች በግሉ ነው ያሳተማቸው፡፡ 1983 . አርቲስቲክ ማተሚያ ቤት የታተመውንትንሳኤመፅሃፍ መታሰቢያነቱን በፋሽስቶችቀይ ሽብርለወደቅው /ለሞተው/ አጎቱ ለታምሩ ተክሉ አድርጓል፡፡ በዚሁ ማተሚያ ቤት 1995 . የታተመውረቂቅ አሻራደግሞ ማስታወሻነቱን ለባለቤቱ ብስራት አሰፋ እና ለልጁ ትንሳኤ ሲሳይ ይሁንልኝ በማለት ነው ለአባቢያን ያበረከተው፡፡
አስመራ ዩኒቨርሰቲ እያለ የስነ ፅሁፍ እና የቲያትር ክበብ መስርቶ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ’’ብዕር አምባ’’ በሚል ስያሜ፡፡ 4 አመት የዩኒቨርሰቲ ተማሪ እያለም ‘’ስዊት ዲስ ኦርደር’’ የሚል ቲያትር ደርሶ ለእይታ አብቅቷል፡፡ ቲያትሩ በአሉላ አባ ነጋ አዳራሽ የታየ ሲሆን በወቅቱም በተመልካች ዘንድ ተወዳጅ ነበር፡፡ በዚህ ቲያትር ላይ ሲሳይም በተዋናይነት ተሳትፏል፡፡

አስመራ ዩኒቨርሰቲ 2 አመት ካስተማረ በኋላ ሙሉ ጊዜውን ለስነ ፅሁፍ በማድረግ ግርዶሽ የተሰኘውን ድርሰቱን አሳትሟል፡፡ ይህ መፅሃፍም ሰመመንቀጥሎ ከፍተኛ ሽያጭ ነበረው ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥም 40 ቅጃዎች ተሸጦለታል፡፡ ደራሲና መምህር ሲሳይ ንጉሱ 10 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በዋና ፀሀፊነት አገልግሏል፡፡ ካለፉት የተወሰኑ አመታት ጀምሮ ደግሞ ውጪ ከሚገኙ ወዳጆቹ እና ጓደኞቹ ጋር በመሆን አንድነት ኢነተርናሽናል /ቤትን ከፍተው በአመራርነት እየሰራ ይገኛል፡፡ ደራሲ ሲሳይ ንጉሱ 1991 . ከኢትዮጵያ ስነ ጥበባት እና መገናኛ ብዙሃን ሽልማት ድርጅት በስነ ፅሁፍ ዘርፍ ተሸላሚ ነበር፡፡በወቅቱም 20 ብር፣ የክብር ዲፕሎማ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተበርክቶለታል፡፡ በያዝነው አመትም በትምህርት አስተዳደር እና አመራር የማስተርስ ዲግሪውን አግኝቷል፡፡ ስለ ደራሲና መምህር ሲሳይ ንጉሱ እኔ ከአንደበቱ የሰማሁትን ይህን አካፈልኳችሁ ቀሪውን ደግሞ እናንተ ጨምሩበት……….   !!!!

ድንበር ያልገደበው ፤ ወሰን ያልተበጀለት የ 96 ዓመታት የሰውነት ጉዞ ተቋጨ። ---- ዶክተር ካትሪን ሐምሊን

ዶክተር ካትሪን ሐምሊን 96 ዓመታቸው መጋቢት 9፣2012ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። / ካትሪን ሀምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ(Hamlin Fistula Ethiopia) የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በማቋቋም ከ60 አመታት በላይ የፌስቱላ ህክምናን በመስጠት ይታወቃሉ። የማህጸን ሀኪም የሆኑት / ካትሪን ሀምሊን 65 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊ በፌስቱላ የተጠቁ ሴቶችን ከስነልቦናዊ እና አካላዊ ቁስለት ለማዳን ችለዋል።ዶክተር ካትሪን ሀምሊን በትውልድ አውስትራሊያዊ ቢሆኑም ለኢትዮጵያ ባደረጉት ውለታ (የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ችግርን በመቅረፋቸው) የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።
አዋላጆችን ለማሰልጠን ከሀገራቸው አውስትራሊያ የመጡት ዶ/ር ካትሪን ሀምሊን እዚሁ ኢትዮጵያ በመቅረት ለመጀመሪያ ጊዜ የፊስቱላ ህክምና ብቻ የሚሰጥባቸው ተቋማትን በመመስረት ሰፊ ስራ ሰርተዋል፡፡ በዚህ ረገድም በኢትዮጵያ በመላ ሀገሪቱ ወደ 6 የሚጠጉ የፊስቱላ ህክምና አገልግሎት መስጫዎችን አቋቁመዋል፡፡ በአዲስ አበባ ፣በባህር ዳር እና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች እና ክልኒኮች ጋር የተጣመሩ ከአምስት መቶ ሀምሳ በላይ የሕክምና ባለሙያዎችን ያፈራው የዶ/ ሪግራንድ እና / ካትሪን የፊስቱላ መታሰቢያ ተቋም በሚያደርጋቸው ምግባረ ሰናይ ተግባራት በአውስትራሊያ እና በተለያዩ አለማት ከፍተኛ እውቅና ለማግኘት ችሏል።

የሴቶቹ ሕይወት ሲለወጥና ሲታደስ አያለሁ፡፡ ሁሌም ሃሳቤ ከነሱ ጋር ነው፤ ህመማቸው ህመሜ ነው፡፡ ይሄ ደሞ የምችለውን እንድሰራና እንዳደርግ ይገፋፋኛል፡፡ እስከዛሬ እዚህ የኖርኩትና አሁንም እዚህ የምኖረው በዚህ ምክንያት ነው  / ካትሪን ሃምሊን
 አውስትራሊያዊቷ / ካትሪን ሀምሊን እና ባለቤታቸው / ሬጂና ሀምሊን ወደ ኢትየጵያ ሲመጡ ሀሳባቸው የአጭር ግዜ ቆይታ ለማድረግ ነበር፡፡ የመጀመሪያዋን የፊስቱላ ታማሚ ስቃይ ካዩ በኋላ ግን ሁሉ ነገር ተለወጠ፡፡ ወደ አውስትራሊያ መመለሱን ተውት፡፡ ውብ አጸድ ባለው ፊሰቱላ ሆሰፒታል ግቢ መኖሪያቸውን አድርገው ህይወታቸውን በሙሉ በፊስቱላ የተጎዱ ኢትየጰያውያን እህቶችን ለመርዳት አላማ ለመስጠት ወሰኑ- አደረጉትም፡፡
 
60 አመት መሉ ያለመታከት በፊስቱላ ችግር የሚሰቃዩትን አከሙ::አብረው ጥልፍ አየጠለፉ፣ የእጅ ሙያ እያስተማሩ የስጋ ብቻ ሳይሆን በደረሰባቸው መገለል እና መሸማቀቅ የመንፈስ ስብራት የደረሰባቸውን እህቶች በሩህሩነት እና ጥልቅ ፍቅር በተሞላ እንክብካቤ አዲስ ህይወት ሰጡ፡፡ የኔ ጥረት ብቻ አይበቃም ብለው ተጣጥረው አዋላጆችን የሚያሰለጥን ኮሌጅ ከፍተው ብዙዎችን ባለሙያ አደረጉ፡፡ ተቆጥሮ የማያልቅ ደግነት፣ የሙያ ፍቅር እና ርህራሄ የታደሉት ሀምሊን ለኢትዮጵያ ብዙ ደክመዋል፡፡ እድሜ ያልገደባቸው ዶ/ር ካትሪን የእርጅና ድካም ሳያሸንፋቸው ሲሰሩ ነበር፡፡ 
በእኔ አድሜ ፊስቱላ ላይጠፋ ይችላል በእናንተ እድሜ ግን ይቻላልሲሉም በአንድ ወቅት / ሀምሊን ለወጣቶች ተናግረው ነበር፡፡ በተጨማሪም ዶ/ር ካትሪን ሀምሊን “ ሰው ስለራሱ ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ ስለሌላውም እየተጨነቀ እንዲኖር በሚያስችል መልኩ የተቃኘውን ኢትዮጵያዊ አኗኗር ” ያደንቁም ነበር፡፡
በማንኛውም ህብረተሰብ ውስጥ በህመማቸው ወይ በሌላ ምክንያት ከተገፉ፣ከተገለሉ እናም በዚህ ምክንያት ተስፋቸው ከጨለመ ወገኖች ጋር ከመቆም የላቀ ሰብአዊነት የለም፡፡ መልካም ተግባር ሁሌም ከመቃብር በላይ እንደሆነ የኢትዮጵያ እና የሴት ልጆቿ የክፉ ቀን ባለውለታዎች የሆኑት / ካትሪን እና ሟቹ ባለቤታቸው / ሪግራንድ በተግባር አስመስክረዋል። ለሦስት አመታት የሥራ ኮንትራት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከስድሳ አመታት በላይ ጉልበታቸውን ፣እውቀታቸውን ገንዘባቸውን እና ህይወታቸውን ጭምር ለኢትዮጵያ እና ለልጆቿ በገጸ በረከት ያበረከቱት / ካትሪን እና ባለቤታቸው አንድ ወንድ ልጅ ያፈሩ ሲሆን የአራት ልጆችም አያቶች ለመሆን በቅተዋል። 

ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ህይወታቸውን የሰጡ ታላቅ እናት …..!!!