Sunday, November 3, 2013

አየር መንገዱ የአፍሪካ ምርጥ ተብሎ ተሸለመ

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአህጉሪቱ ምርጥ አየር መንገድ ተብሎ ለመሸለም የበቃው በአፍሪካ ካሉ አየር መንገዶች ጋር ተወዳድሮ በማሸነፉ ነው፡፡

 አየር መንገዱ ከዚህም በተጨማሪ በአህጉሪቱ ምርጥ የአውሮፕላን ሰራተኞችን ሽልማትንም ጭምር ያሸነፈ ሲሆን ሽልማቱንም በናይጄሪያ ሌጎስ በተደረገ ዝግጅት ላይ ተቀብሏል።  በተመሳሳይ የቦሌ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያም በምስራቅ አፍሪካ ምርጡ የአውሮፕላን ማረፊያ ተብሎ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

 በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለምአቀፍ አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ወልደማሪያም እንዳሉት ሽልማቱ ባለፉት 70 ዓመታት አየር መንገዱ ለአህጉሪቱ ላበረከተው አገልግሎት ህያው ምስክር ነው ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አያይዘውም አየር መንገዱና የቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለሶስቱም ሽልማት የበቁት ለአፍሪካ ብሎም ለአለምአቀፍ ተገልጋዮች ጥራቱን የጠበቀ የደንበኞች አገልግሎት በመስጠቱ እንደሆነ ነው የገለፁት፡፡ በአሁኑ ሰዓትም አየር መንገዱ በአፍሪካ 47 መዳረሻዎች አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል፡፡
                                                                                          
                                                                                  ምንጭ:  ዚስ ደይ ላይፍ

No comments:

Post a Comment