Sunday, November 24, 2013

ኢትዮጵያ የናሚቢያን የጤና ባለሙያዎች ልታሰለጥን ነው

ኢትዮጵያ የናሚቢያን የጤና ዶክተሮች፣ ነርሶችና ቴክኒሻኖችን ጨምሮ የተለያዩ  ባለሙያዎችን ልታሰለጥን ነው ። ናሚቢያ የስልጠና ድጋፉን ማግኘት የሚያስችላትን  ስምምነትንም  ከኢትዮጵያ  ጋር ተፈራርማለች።

   በስምምነቱ መሰረትም ናሚቢያውያን ባለሙያዎች በኢትዮጵያ የሚሰለጥኑ ሲሆን፥ ቀጣይነት ያለው የነፃ  ትምህርት እድል ለአገራቱ ዜጎች ኢትዮጵያ የምትሰጥ ይሆናል። ስምምነቱን የኢፌዴሪ  የጤና  ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ  እና በናሚቢያ አቻቸው ሪቻርድ ካምዊ መካከል ተፈርሟል።
    በፊርማው ስነ ስርዓት ላይም ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ ፥ ኢትዮጵያ በጤና  ኤክስቴንሽነን መርሃ ግብር ዘርፍ ለናሚቢያ ለምዶቿን በማካፈል ድጋፍ ስታደርግ  መቆየቷን አንስተዋል ። በሽታን በመከላከሉ በርካታ  ስኬቶችን ኢትዮጵያ ማስመዝገቧን ያነሱት ሚኒስትሩ፥  ይህን ልምዷን ለናሚቢያ ማካፈል  ትፈልጋለች ብለዋል።
    ኢትዮጵያ  እና ናሚቢያ ተመሳሳይ የሆኑ የበሽታ ዓይነቶች በአገራቸው እንዳሉ ያነሱት ሪቻርድ ካምዊ፥ በተለይም በገጠር አከባቢዎች የጤና ባለሙያዎች እጥረት ግን  ለአገራቸው ፈተና ሆኖ  መቆየቱን  አመልክተዋል። በአሁኑ ወቅት በአምስት የናሚቢያ ግዛቶች  በሙከራ ደረጃ  እየተካሄደ ላለው የጤና  ኤክስቴንሽን መርሃ ግብር ኢትዮጵያ  ስልጠና በመስጠትና ልምድ በማካፈል ድጋፍ  እያደረገች ነው።
                                                                                  ምንጭ፦ http://www.namibian.com.na

No comments:

Post a Comment