Sunday, November 24, 2013

አዲስ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ኢንዱስትሪውን ተቀላቀለ

 በአዲስ አበባ ከ700 መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል ተመረቀ። ከፍተኛ ቴክኖሎጂዎች እንደተገጠሙለት የተነገረለት ይህ ባለ አስር ፎቅ ሆቴልን ገንብቶ ለማጠናቀቅ አምሰት ዓመታትን ፈጅቷል።

  ሆቴሉ እስከ 700 ያህል ሰዎችን ሊያስተናግዱ የሚችሉ 7 የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ አምስት ሬስቶራንቶች፣ የመዋኛ ገንዳና ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎችን ይዟል። በምረቃው ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ፥ ከተማዋ ያለባትን ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል እጥረት በመቅረፍ በኩል አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ሆቴሉ ለ350 ሰዎች ቋሚ የስራ እድል ይፈጥራል።

No comments:

Post a Comment