የዋዜማ በዓሉ ላይ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ እንደገለፁት፥ ከዚህ ቀደም በ24 ሰዓት ከፍተኛ የአርማታ ሙሌት በማካሄድ
የአለም ሪኮርድ
የተመዘገበው በቻይና ሀገር
የሃይል
ማመንጫ
ግንባታ
ሲሆን፥ መጠኑ 16 ሺህ 800 ሜትር
ኪዩብ
ነበር።ህዳር
20 ቀን 2007 ዓ.ም በህዳሴው ግድብ ፕሮጀክት በተካሄደ
የአርማታ
ሙሌት
በ24 ሰዓት
ውስጥ
16 ሺህ 949 ሜትር
ኪዩብ
አርማታ በመሙላት
ኢትዮጵያ ሪከርዱን
መስበር መቻሏን ኢንጂነር ስመኘው ተናግረዋል።
በጠቅላለው 10 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሜትር ኪዩቢከ አርማታ የሚሞላበት የህዳሴው ግድብ ግንባታ ስራው ሲጠናቀቅ 145 ሜትር ከፍታ እና 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ርዝመት ይኖረዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ከ60 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ በላይ ውሃ በመያዝ 6 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌትሪክ ሃይል የማመንጨት አቅም ሲኖረው በትልቅነቱ ከአፍሪካ አንደኛ ከዓለም ደግሞ ሰባተኛ ደረጃን ይይዛል።
No comments:
Post a Comment