ቤተ ማሪያም የቅዱስ ላሊበላ የመጀመሪያ ስራ ስትሆን ታህሳስ 29 የልደት በዓልም በዚች ቤተክርስቲያን ነው በድምቀት የሚከበረው፡፡ ቤተ መድኃኔዓለም በመጠን ከሁሉም የሚበልጥ እና “አፍሮ አይገባ” የተባለው መስቀል የሚገኝበት ነው፡፡ ቤተ ጊዮርጊስ የሚባለው ደግሞ በመስቀል ቅርፅ የታነፀ እና ከሌሎቹ በተለየ ሁኔታ ረቂቅ የኪነ ህንፃ ጥበብ የተከናወነበት ነው፡፡
ቅዱስ ላሊበላ እነዚህን አብያተ ክርሰቲያናት ለማነፅ ከ22 - 30 ዓመታት ፈጅቶበታል ይባላል፡፡ ከ1512 - 1518 ኢትዮጵያን የጎበኘው የፖርቹጋል ቄስ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ /ላሊበላን የጎበኘ የመጀመሪያው አውሮፓዊ/ እንዲህ ብሎ ነበር፡-
“ስለ ላሊበላ ፍልፍል አብያተ ክርስቲያናት ስራዎች ብዙ ብፅፍ የሚያምነኝ ሰው መኖሩ በጣም ያሳስበኛል፤ያስጨንቀኛል፡፡ እስካሁን ያልኩትንም እንኳን ቢሆን “ውሸት ነው” የሚሉኝ፡፡ ነገር ግን የፃፍኩት በሙሉ እውነት ለመሆኑ በኃያሉ እግዛብሔር ስም እምላለሁ፡፡ እንዲያውም ከዚህ በላይ ማለት ይቻላል፡፡ ሆኖም በቀጣፊነት ስሜ እንደማይነሳ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡”
ምንጭ ፡- ህብር ኢትዮጵያ መፅሃፍ
No comments:
Post a Comment