ዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጎርጎሮሳውያኑ 2014 ምርጥ
አትሌቶችን ለመምረጥ የዕጮዎችን ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያ በገንዘቤ ዲባባ ብቻ ተወከለች፡፡
ገንዘቤ በምርጫው ዕጩ ለመሆን የበቃችው በተያዘው የጎርጎሮሳውያን ዘመን በ1 ሺህ 500 ፣ በ2 ሺህ፣ በ3 ሺህ፣ በ5 ሺህ ሜትሮች እና በ2 ማይል ርቀት ባስመዘገበችው ውጤት ነው፡፡ ከዚህ ውጭም በቤት ውስጥ ውድድሮች በ1 ሺህ 5 መቶ እና 3 ሺህ ሜትሮች እንዲሁም በ2 ማይልስ ርቀት ያስመዘገበችው ውጤት በዕጩነት አስመርጧታል፡፡
የዕጩዎች
ምርጫ በስድስቱም የዓለም ክፍላተ አህጉራት የሚገኙ ዓለም አቀፍ አትሌቶችን ያካተተ ሲሆን ምርጫውን ያከናወኑት የዓለም አቀፉ
አትሌቲክስ ፓናል ኤክስፐርቶች ናቸው፡፡
በባለሞያዎቹ ምርጫ ለዕጩነት የቀረቡት አትሌቶች በወንዶች እና
በሴቶች አስር አስር ሲሆኑ በሁለቱም ጾታዎች ስድስት አትሌቶች
ይመረጣሉ፡፡
ከቀረቡት
ዕጩዎቹ በሁለቱም ጾታዎች ሶስት ሶስት አትሌቶች የሚለዩት በአትሌቲክሱ ሰዎች ከዛሬ መስከረም 23 ቀን እስከ ጥቅምት 6 ቀን
2007 ዓ.ም በሚካሄድ የኢሜል ድምጽ አሰጣጥ ነው፡፡ ከተመረጡት
ሶስት ሶስት አትሌቶች ውስጥ የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፋውንዴሽን
በሁለቱም ጾታ የጎርጎሮሳውያኑ 2014 የዓለም ምረጥ አትሌት አሸናፊዎችን ሕዳር 12 ቀን 2007 ዓ.ም በሚካሄደው የዓለም
አትሌቲክስ በዓል ላይ ያሳውቃል፡፡
No comments:
Post a Comment